Get Mystery Box with random crypto!

የስርአት ለዉጥ አለመኖሩ ፓርቲዎች በሚገባ መንቀሳቀስ እንዳይችሉ አድርጓል ሲል የፖለቲካ ፓርቲዎች | AHADU RADIO FM 94.3

የስርአት ለዉጥ አለመኖሩ ፓርቲዎች በሚገባ መንቀሳቀስ እንዳይችሉ አድርጓል ሲል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጹ፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በፓርቲዎችና መንግስት መካከል እንዲሁም በብልፅግና ፓርቲ በኩል ያሉትን ችግሮች ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ያለዉ የፖለቲካ ስርአት ያልተለወጠ መሆኑ አዳጋች አድርጎታል ሲሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዋና ፀሀፊ ዶክተር ራሄል ባፌ ገልፀዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እየተንቀሳቀሱ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገራዊ ተሳትፎም ይሁን በፓርቲያቸዉ የዉስጥ ጉዳይ ለመነጋገር፤ አባላትን ለማፍራትና የደጋፊዎቻቸዉን ቁጥር ለመጨመር ጥረት በሚያደርጉበት ወቅት ለወከባና እስር በመዳረጋቸዉ የተነሳ ፓርቲዎች እንዲዳከሙ እያደረገ ነዉ ብለዋል፡፡
ከነበረዉ የኢህ አዲግ ስርአት የፀዳ አሰራር አለመኖሩ ከፍተኛ ችግር ሆኗል ሲሉ አክለዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24