Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለማህበረሰቡ እርዳታዎችን ለማድረግ የሚያስ | AHADU RADIO FM 94.3

በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለማህበረሰቡ እርዳታዎችን ለማድረግ የሚያስችል የአቅም ችግር እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡
በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የዓለም የምግብ ፕሮግራም እና ሌሎች የዓለም የእርዳታ ድርጅቶች በክልሉ የሚያደርጉትን ድጋፍ ከማቋራጣቸው ጋር ተያይዞ ለማህበረሰቡ ለመድረስ ምን እየሰሩ ነው ሲል የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ባለስልጣንን አነጋግሯል፡፡
በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የማህበረሰቡ አካል እንደመሆናቸው ጦርነቱ እነሱንም ጎድቷቸዋል ያሉት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ አብዛኞቹ የሲቪል ማህበራት የገቢ ምንጮቸው ከውጪ በሚዘጋጁ ውድድሮች ላይ ቀርበው በማሸነፍ በሚገኙ እርዳታዎች እና ፈንዶች ነው ያሉ ሲሆን ተንቀሳቅሰው ገንዘብ ለማግኘት እና ውድድሮች ላይ ለመሳተፍ አልቻሉም ብለዋል፡፡
የሲቪል ማህበራቱ በተለያዩ አካባቢዎች ላይ በመንቀሳቀስ ለማህበረሰቡ የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶችን እየሰጡ እና አቅም ያላቸው ማህበራትም አቀም ለሌላቸው እያካፈሉ እና እየተረዳዱ ነው የሚገኙት ብለዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24