Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመር በተደጋጋሚ የሚደርሱትን ችግሮች ለመቀነስ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መ | AHADU RADIO FM 94.3

በኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመር በተደጋጋሚ የሚደርሱትን ችግሮች ለመቀነስ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚንስቴር አስታወቀ፡፡
የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት መስመር ከዚህ በፊት የባቡር መሠረተ ልማት ስርቆት፣ የእንስሳት መጋጨት የባቡር እገታ እና መሠል ችሮች ሲስተዋሉ መቆየታቸዉ ይታወቃል፡፡
አሀዱም ችግሩን ለመፍታት ምን አይነት ስራዎች ተሰሩ ሲል የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚንስቴርን ጠይቋል፡፡
ችግሮችን ለመፍታት የፌደራል ፖሊስ ፤የክልል የፀጥታ አካላት፣እንዲሁም የትራንስፖርት ቢሮዎች ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ስራዎችን ሲሰሩ መቆታቸዉን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚንስትር ዲኤታ አቶ በርኦ ሀሰን ለአሀዱ ተናግረዋል፡፡
ከፍተኛ የደህንነት ስጋት በነበረባቸው የባቡር መስመሮች አካባቢ በተሰራዉ ስራ አሁን ላይ ስጋቱን መቀነስ መቻሉን አስታዉቀዋል፡፡
የባቡር መስመሩ የሚሰጠውን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጥቅም ከፍ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24