Get Mystery Box with random crypto!

በሱሉልታ ከተማ በታጣቂዎች ቁጥራቸው በውል ያልታውቁ ሰዎች ታፍነው ተወስደዋል በሚል እየተዘዋወረ ያ | AHADU RADIO FM 94.3

በሱሉልታ ከተማ በታጣቂዎች ቁጥራቸው በውል ያልታውቁ ሰዎች ታፍነው ተወስደዋል በሚል እየተዘዋወረ ያለው መረጃ ሀሰተኛ እንደሆነ ተገለጸ፡፡
በቅርቡ በተዋቀረው የሸገር ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኘው የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች መንግስት ሸኔ ብሎ በሚጠራው ቡድን ታጣቂዎች ታፍነው መወሰዳቸውን የሚገልጹ መረጃዎች በተለያዩ የማህበራዊ ድህረ ገጾች ላይ ሲዘዋወሩ እንደነበር ይታወሳል፡፡
የተወሰዱት ሰዎችም ያሉበት እንደማይታወቅ እና አጋቾችም ይህን ያህል ብር አምጡና እንለቃቸዋለን በማለት እየተደራደሩ እንደሚገኙ መዘገቡም ይታወቃል፡፡
ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ ያለውን ነባራዊ እውነታ እንዲያብራሩ አሃዱ ያነጋገራቸው የሸገር ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ናስር ሁሴን ከተማ አስተዳድሩ መረጃው ከወጣ በኋላ የማጣራት ስራዎችን እንደሰራ አንስተው ሆኖም በከተማ መስተዳድሩ ውስጥ በሚገኙ ክፍለ ከተሞች ውስጥ ታፍነው የተወሰዱ ዜጎች አለመኖራቸውን ተናግረዋል፡፡
ሃላፊው አክለውም በማህበራዊ ሚዲያዎች እየወጡ ያሉት ዘገባዎች ከእውነት የራቁ እና ተአማኒነት የሌላቸው መሆናቸውን በመግለጽ ህብረተሰቡን በተሳሳቱ ዘገባዎች ማደናገር ተገቢ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24