Get Mystery Box with random crypto!

በአገር አቋራጭ መንገዶች ላይ የሚስተዋሉ የደህንነት ስጋቶችን ለመፍታት ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ | AHADU RADIO FM 94.3

በአገር አቋራጭ መንገዶች ላይ የሚስተዋሉ የደህንነት ስጋቶችን ለመፍታት ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የቅንጅት ስራ መጀመሩ ተገለፀ፡፡
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ አገር አቋራጭ መንገዶች ላይ በታጣቂዎች የሚደርሱ እገታዎች እንዲሁም ጥቃቶችን ተከትሎ አሽከርካሪዎችም ሆኑ ተሳፋሪዎችን ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንዲወድቁ አድርጓል፡፡ ፡፡
የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ምክትል ፕሬዘዳንቶች እንዲሁም የትራንስፖርት ቢሮ እና የፀጥታ ቢሮ ሀላፊዎችን ያሳተፈ ሰፊ ውይይት በማድረግ የቁጥጥር ስራውን በማጠናከር መንገዶቹ ሰላማዊ እንዲሆኑ የማድረግ ስራዎች መጀመራቸውን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚንስቴር ሚኒስትር ዴኤታው አቶ በርኦ ሀሰንን አነጋግሯል አስታውቀዋል፡፡
አክለውም በተወሰኑ አካባቢዎች ላይ በወጪ እና ገቢ ንግድ ትራንስፖርት ላይ ብቻ የሚሰሩ አገር አቋራጭ የጭነት ተሸከርካሪዎች ላይ መንገድ በመዝጋት እና ላልተፈለጉ አላማዎች እንዲሁም በግዳጅ የተለያዩ የአገር ውስጥ ጭነት አገልግሎቶች እንዲውሉ ማድረግን የመሰሉ ህገ ወጥ ተግባራት እንደሚስተዋሉ ገልፀዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24