Get Mystery Box with random crypto!

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ልኡካን ወደ አማራ ክልል መግባታቸው የሁለቱን ክልሎች ግንኙነት | AHADU RADIO FM 94.3

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ልኡካን ወደ አማራ ክልል መግባታቸው የሁለቱን ክልሎች ግንኙነት ለማጠናከር ጥሩ ጅማሬ መሆኑ ተገለፀ፡፡
በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርእሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ የሚመራ ልዑክ ከአማራ ክልል መስተዳድር እነ የቢሮ ሃላፊዎች ጋር በባሕር ዳር ዉይይት ማድረጉ ይታወቃል፡፡ በሁለቱ ክልሎች መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ ሆነ ዳግም ግጭት እንዳይፈጠር ምን አይነት አስተዋጾ አለዉ ሲል አሐዱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን አነጋግሯል፡፡
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ወደ አማራ ክልል መሄዳቸው በሁለቱ ክልሎች መካከል ያለውን ዉጥረት ሰላም ለማስፈን እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ለማጠናከር ጥሩ የሚባል ጅማሮ ነው ብለዉ ሰላምን ለማስፈን ከዚህም በላይ ግንኙነቶችን ማጠናከር አስፈላጊ ነው ያሉት የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ አባል ኮማንደር ገብረመስቀል ገብረሚካኤል ናቸው፡፡
ሆኖም የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በሚጠበቀው መልኩ አለመተግበሩ አሁንም ለክልሎቹ አንዱ ችግር መሆኑን አንስተዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24