Get Mystery Box with random crypto!

አደገኛ አውሎ ነፋስ በመጪው ሀሙስ የህንድን ምዐራባዊ ዳርቻ ሊመታ እንደሚችል ተሰግቷል፡፡ በሀገሪቱ | AHADU RADIO FM 94.3

አደገኛ አውሎ ነፋስ በመጪው ሀሙስ የህንድን ምዐራባዊ ዳርቻ ሊመታ እንደሚችል ተሰግቷል፡፡
በሀገሪቱ ምዕራባዊ የባህር ዳርቻ እያደገ የመጣው ማዕበል ወደ ሀይለኛ አውሎ ነፋስነት ሊቀየርና የጉጅራትን ግዛት እንዲሁም የፓኪስታንን ደቡባዊ አካባቢዎች ሊመታ ይችላል ነው የተባለው፡፡
ቢፓ ርጆሪ ተብሎ የተሰየመው አውሎ ነፋስ የፊታችን ሀሙስ ሊከሰት እንደሚችል እና ከ125 እስከ 135 ኪሎሜትር በሰዓት እንደሚጓዝ የህንድ አየር ትምበያ መስሪያ ቤት በትላንትናው እለት አሳውቋል፡፡
የአየር ንብረት መስሪያ ቤቱ አሳ አጥማጆች ስራቸውን እንዲያቆሙ እና ማህበረሰቡም አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ ማሳሰቢያ መስጠቱም ተነግሯል፡፡
እያደገ በመጣው ከባድ የአየረ ጸባይ ምክንያትም በጉጂራት ወደብ ስራዎች እንዲቋረጡ መደረጉን በወደቡ የተሰማራ አንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ ኩባንያ ማሳወቁም ተጠቁሟል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24