Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ ዉስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሻጋሪ የሆነ ስርአት መዘርጋት ላይ ተኩረት አድረ | AHADU RADIO FM 94.3

በኢትዮጵያ ዉስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሻጋሪ የሆነ ስርአት መዘርጋት ላይ ተኩረት አድረገዉ ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡
ሀገሪቱ በተለያዩ ጊዜያት የሚያጋጥሟት አለመረጋጋቶች እና የጦርነት አዙሪቶች በሙሉ ከፖለቲካዋ ስርአት ጋር መያያዙ እንደ ዋና መንስኤነት ይነሳል፡፡
ለዚህ ደግሞ ግንባር ቀደም ተጠያቂ የሚሆኑት የለቲካዉ ስርአት ላይ ከፊት የተቀመጡ የፓርቲ አመራሮች ናቸዉ ያሉት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶክተር መብራቱ አለሙ ናቸው፡፡
በሀገሪቱ ታሪክ ሁሉም ፓርቲዎች ስልጣንን እና ሃብትን የመካፈል ፍላጎትን ከፊት አድርገዉ መነሳታቸዉ ችግሩን አክብዶታል ሲሉ ይገልፃሉ፡፡
አክለዉም በሀገሪቱ ያለዉን ሰላም እና መረጋጋት በዘላቂነት ለማስፈን የፖለቲካ ጥቅምን ከማስቀደም ይልቅ ዘላቂ የሆነ ፡ ለትዉልድ የሚሻገር የአሰራር ስርአትን መዘርጋት ላይ መስራት ይገባቸዋል ሲሉም አክለዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24