Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ክልል ሰሜን ምእራብ ዞን እና አዲ ዳአሮ ወረዳ አካባቢ ከፍተኛ የሆነ የማእድን ዘረፋ እና | AHADU RADIO FM 94.3

በትግራይ ክልል ሰሜን ምእራብ ዞን እና አዲ ዳአሮ ወረዳ አካባቢ ከፍተኛ የሆነ የማእድን ዘረፋ እና የኮንትሮባንድ ንግድ እንዳለ ተገለጸ፡፡
የአዲ ዳአሮ ከተማ ከንቲባ አቶ ተፈሪ ሀይለመለኮት ሰሜን ምእራብ ዞን እና የአዲ ዳአሮ ዞን አካባቢ ከፍተኛ የሆነ የማእድን ዝርፊያ እንዳለ ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡
በተለይ ከፍተኛ የሆነ የወርቅ ክምችት በአካባቢዎቹ በመኖሩ ሰፊ የሆነ የኮንትሮባንድ ዝርፊያ እና ንግድ እንዳስቸገራቸው እና ወንጀሉን ለመቆጣጠር ክልሉ ካሉበት የጸጥታ ችግሮች አንፃር ቁጥጥሩን ፈታኝ እንዳደረገባቸው ጨምረው ተናግረዋል፡፡
ከንቲባው እነዚህ የማእድን ሀብቶች በአግባቡ ጥቅም ላይ ቢውሉ ለክልሉም ሆነ ለሀገሪቱ የሚጠቅሙ ናቸው ያሉ ሲሆን ፣ ዘረፋው እና የኮንትሮባንድ ንግዱ እስከ ኤርትራ እና ሱዳን የሚደርሱ ትላልቅ መረቦች አሉት ብለዋል፡፡
ይህ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ ለማዕድን ዘርፉ ማደግ እንቅፋት እየሆነ መምጣቱን ገልጸው፤ ዘርፉን ለመታደግ እና ሀገር ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ተገቢውን ጥቅም እንድታገኝ ተገቢው የድንበር ጥበቃ እንዲደረግና አስፈላጊው ትኩረት እንዲሰጠውም አስገንዝበዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24