Get Mystery Box with random crypto!

የቤት ግብር ማሻሻያው የተደረገው መንግስት ላይ ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች በመኖራቸው ነው ተ | AHADU RADIO FM 94.3

የቤት ግብር ማሻሻያው የተደረገው መንግስት ላይ ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች በመኖራቸው ነው ተብሏል፡፡
በቅርቡ ይፋ የተደረገውን የቤት ግብር ማሻሻያ አስመልክቶ በርካታ ሃሳቦች ይደመጣሉ፡፡ ከነዚህም መካከል በአሁኑ ወቅት በዜጎች ላይ ከሚታየው ምጣኔ ሃብታዊ ጫና አንጻር ማሻሻያው ወቅታዊ አይደለም የሚሉ ሃሳቦች ሲነሱ ይደመጣል፡፡
ይህን ጉዳይ አስመልክቶ አሃዱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ የንብረት ግብር ማስተግበርያ ጊዜያዊ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት አስተባባሪ አቶ አስማማው ሙሉጌታን አነጋግሯል፡፡
የያዝነው ዓመት ብዙ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች የተነሱበት እንደነበር ጠቅሰው እነዚህን የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ለመፍታት ደግሞ ግብር መክፈል ዋነኛ መፍትሄ በመሆኑ ከዚህ በፊት ለረጅም ጊዜ ተግባራዊ ሲደረግ የቆየው ነባር አዋጅ ላይ ማሻሻያ ተደርጓል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ለዚህም የንብረት ባለቤቶች አንጻራዊ በሆነ መንገድ የተሻለ የመክፈል አቅም አላቸው ያሉ ሲሆን ባለቤቶቹ እንደንብረታቸው መጠን እንዲከፍሉ እየተደረገ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የመክፈል አቅምና ገቢ የሌላቸው ከሆኑ በየወረዳው እየተገመገመና እየቀረበ ነጻ የሚሆኑበት ወይም ምህረት የሚደረግበት አሰራር እንዳለም በአዋጁ ተቀምጧል ብለዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24