Get Mystery Box with random crypto!

በአማራ ክልል የሚታየውን ችግር ለመቅረፍ በክልሉ ቁርጠኛ ሆኖ የሚታገል አመራር የለም ሲሉ በአማራ | AHADU RADIO FM 94.3

በአማራ ክልል የሚታየውን ችግር ለመቅረፍ በክልሉ ቁርጠኛ ሆኖ የሚታገል አመራር የለም ሲሉ በአማራ ክልል የምክር ቤት የአብን አባላት ገለጹ፡፡
በአማራ ክልል ምክር ቤት የሚሳተፉ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) አባላት ወቅታዊ የክልሉን ሁኔታ አስመልክተው መግለጫ ማውጣታቸው ይታወሳል፡፡
እናንተስ በምክር ቤት አባልነታችሁ በመግለጫችሁ ቀሳችዃቸውን ችግሮች ለመቅረፍ ምን እየሰራችሁ ትገኛላችሁ ሲል አሃዱ አባላቱን አነጋግሯል፡፡
ምክር ቤቱ በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ እንደተቀመጠው በዓመት ዝቅተኛ የሚሰበሰበው ለሶስት ጊዜያት በመሆኑ አባላቱን በንቃት በማሳተፍ አስፈጻሚውን ቀርቦ ለመገምገምም ሆነ የህዝቡን ችግር በየጊዜው እየገመገሙ ለመፍታት የሚያስችል ግንኙነት የለንም ያሉት በአማራ ክልል ምክር ቤት የአብን ተወካይ እና የባህር ዳርና አካባቢው አስተባባሪ ዶክተር በቃሉ ታረቀኝ ናቸው፡፡
በክልሉ ባለው መዋቅርም ለአማራ ክልል ህዝብና በክልሉ ላሉት ችግሮችም በቁርጠኝነት የሚታገል አመራር አለ ብሎ ለመናገር የሚያስደፍር አይደለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24