Get Mystery Box with random crypto!

ውይይት አድርጎ ወደ ስራ ለመግባት ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ደብዳቤ ተፅፎ ምላሽ እየተጠባ | AHADU RADIO FM 94.3

ውይይት አድርጎ ወደ ስራ ለመግባት ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ደብዳቤ ተፅፎ ምላሽ እየተጠባበቀ መሆኑን ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ አስታወቀ።
በምክክሩ አስፈላጊነትና አካሄድ ላይ ዉይይት አድርጎ ወደ ስራ ለመግባት ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ደብዳቤ ተፅፎ ምላሽ እየተጠባበቀ መሆኑን ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ አስታዉቋል፡፡
የትግራይ ክልልን ጨምሮ በሁሉም ክልሎች በሚገኙ ወረዳዎች የተሳታፊዎች ልየታና አጀንዳ የማሰባሰብና የመረጣ ስራ አስቸጋሪ ሁኔታ ካላጋጠመ በስተቀር የ2015 ዓ.ም ከመጠናቀቁ በፊት እንደሚጠናቀቅ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ አንዱ ኮሚሽነር እና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊዉ ዶክተር ዮናስ አዳዬ ለአሀዱ ተናግረዋል።
ከጊዜዊ አስታዳደሩ ለተፃፈዉ ደብዳቤ ምላሽ ሲገኝ ስራዎችን እንደሚኪያከናዉኑ አስታዉቀዋል፡፡
በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ደረጃ ለሚደረጉ የአጀንዳ ማሰባሰብ ስራዎች ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎች ሁለት ሁለት ተወካዮችን ይመርጣሉ ብለዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24