Get Mystery Box with random crypto!

በጊኒ በተደረገ ምርጫ የተቀናቃኝ ፓርቲዎች ጥምረት አሸንፏል፡፡ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኡማሮ ሲሶኮ እ | AHADU RADIO FM 94.3

በጊኒ በተደረገ ምርጫ የተቀናቃኝ ፓርቲዎች ጥምረት አሸንፏል፡፡
የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኡማሮ ሲሶኮ እምባሎ ከአንድ አመት በፊት የቀድሞውን ብሄራዊ ምክርቤት ካፈረሱ በኋላ በተደረገው የመጀመሪያ ምርጫ የተቀናቃኝ ፓርቲዎች ጥምረቱ ብዙውን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ እንዳገኘ ተነግሯል፡፡
የአምስት ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው ጥምረቱ ባሳለፍነው እሁድ በተደረገው ምርጫ ከ102 አጠቃላይ መቀመጫዎች ሀምሳ አራቱን ማሸነፉ ነው የተዘገበው፡፡
የፕሬዝዳንት እመባሎ ፓርቲ በበኩሉ ሀያ ዘጠኝ መቀመጫዎችን ብቻ ማግኘቱን የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን ይፋ ባደረገው የድምጽ ቆጠራ ውጤት ታውቋል፡፡
አሁን ባለው የሀገሪቱ የፖለቲካ ስርዓት አብላጫ ድምጽ ያገኘው ፓርቲ ወይም ጥምረቱ አስተዳደር መመስረት የሚችል ሲሆን በአንዳንድ ሁኔታዎች ግን ፕሬዝዳንቱ አስተዳደሩን ሊያፈርሱት እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24