Get Mystery Box with random crypto!

ከጤና መድህን አገልግሎት የሚሰበሰበውን ክፍያ ወደ አንድ ቋት ለማስገባት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተ | AHADU RADIO FM 94.3

ከጤና መድህን አገልግሎት የሚሰበሰበውን ክፍያ ወደ አንድ ቋት ለማስገባት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገለፀ፡፡
ለጤና መድህን አገልግሎት ተብሎ ከአባላት መዋጮ ከሚሰበሰብ ገንዝብ ውስጥ ወደ ባንክ የማይገባ እና በቀበሌ አመራሮች እጅ ገብቶ ለተፈለገለት አላማ ሳይውል የሚቀር ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ መኖሩ መገለጹ የሚታወስ ነው፡፡
አሐዱም ስለጉዳዩ የኢፌድሪ ጤና መድህን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አማካሪ አቶ ዳምጠው ጥላሁን አነጋግሯል፡፡
በዋና መስሪያ ቤቶች እና በቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች ላይ የተሰራው የኦዲት ሪፖርት የ2013ዓ.ም የነበረውን ነው ያሉ ሲሆን የማህበረሰብ የጤና መድህን የአንድ አመት መድህን በመሆኑ የሚሰበሰበው የገንዘብ መጠንም በአባላት ቁጥር ላይ ተመርኩዞ ነው ብለዋል፡፡
የኦዲት ሪፖርቱ አዲሱ የጤና መድህን ተጠቃሚነት አባል የመሆን አስገዳጅ አዋጅ ሳይወጣ በፊት ስለነበረ ይሰበሰባል የተባለው የገንዘብ መጠንም በመድህኑ ተጠቃሚ አባል ቁጥር ላይ በመሆኑ ላይሳካ ይችላል ያሉ ሲሆን በ2014ዓ.ም አስገዳጅ አዋጁ ከወጣ በኃላ መሻሻሎች እንዳሉ እና በቀጣይ በ2016ዓ.ም የተስተዋሉ ችግሮችን እና የአፈጻጸም ጉድለቶችን በመገምገም የክፍያ አሰባሰብ ስርአቱ ላይ ማሻሻያዎች እና ለውጦችን በማድረግ የገንዘብ አሰባሰብ ሂደቱን በአንድ ቋት ለማድረግ እቅድ ይዘው እየተንቀሳቀሱ ነው ብለዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24