Get Mystery Box with random crypto!

በዜጎች ላይ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማስቆም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፍትህ እ | AHADU RADIO FM 94.3

በዜጎች ላይ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማስቆም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፍትህ እና የህግ ቋሚ ኮሚቴ ሀላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
የሰብዓዊ መብት ኮምሽን በዜጎች ላይ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በተመለከተ አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድ በተለያየ ጊዜያት ሪፖርት እና መግለጫዎችን ያወጣል፡፡
መንግስት የሰብዓዊ መብት ጥሰት በዜጎች ላይ ከተፈጸመ በኃላ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ከመፈጸሙ አስቀድሞ የመከላከል ስራ መስራት እንዳለበት ለአሀዱ የተናገሩት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ፎረም ዋና ዳይሬክተር አቶ ተረፈ ጠጌቲ ናቸው፡፡
የሰብዓዊ መብት ኮምሽን እና ሌሎች ተቋማትን ጨምሮ በሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ የሚያወጡትን ሪፖርት ወስዶ ችግሩን ከመፍታት ይልቅ ክልሎችን ጨምሮ ተቃራኒ የሆነ ምላሽ የመስጠት ሁኔታዎች ይስተዋላል ነው ያሉት፡፡
በኮምሽኑም ሆነ በመንግስት በኩል የሚወጡ የተለያዩ መግለጫዎችና ሪፖርቶች ማህበረሰቡ ላይ ግራ መጋባትን የሚፈጥር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የሰብዓዊ መብት ኮምሽን የሚያወጣው ሪፖርት በመንግስት በኩል ተግባራዊ እንዲሆን የጋራ አሰራርን ለመዘርጋት እንዲቻል የህዝብ ተወካይዎች ምክር ቤት የፍትህ እና የህግ ቋሚ ኮሚቴ መመሪያ በማዘጋጀት ሀላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24