Get Mystery Box with random crypto!

ለሙስሊሟ እህቴ

የቴሌግራም ቻናል አርማ lemuslimuaehte — ለሙስሊሟ እህቴ
የቴሌግራም ቻናል አርማ lemuslimuaehte — ለሙስሊሟ እህቴ
የሰርጥ አድራሻ: @lemuslimuaehte
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.56K
የሰርጥ መግለጫ

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ
بسم الله الرحمن الرحيم
በቻናላችን
ዲናዊ እውቀቶች
መሳጭ የሆኑ ታሪኮች
ስለ ትዳር ምክሮች

እናንተን ያዝናናል ያስተምራል የምንላቸው
በአላህ ፍቃድ ለናንተ እናደርሳለን።
ከናንተ ሚጠበቀው join ማረግ ነው።
@lemuslimuaehte
for any comment 👇
@fitayebot

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-02 06:38:49 ❥:::::::እባክሽን ታጋሽ ሁኚ:::::::::❥
·
#በጣም የሚዋደዱ በኢማናቸው ጠንካሮች የሆኑ ባለትዳሮች ነበሩ። አንድ ቀን ሚስት ከባሏ እና ከቤተሰቦቿ ጋር የማምሸት ፕሮግራም ትይዝና ለቧሏ ቀድማ ትነግረዋለች። ባል ግን በዛ ቀን ከቀጠሮው ሰአት አሳልፎ እንደውም ያመሻል።
·
ሚስት ስትደውል ስልኩ አይሰራም። በጣም ትናደዳለች። ባልም አምሽቶና ደክሞት ቤት ሲገባ ሚስቱም «ከቤተሰቦቼ መቅረቴ ሲገርመኝ እንዲህ አምሽተክ ትመጣለክ? ለምን አታድርም ነበር ...... ?» በጣም ጮክ ብላ ትናገረዋለች ባል የሆነውን ሊያስረዳት ቢሞክርም ልትሰማው አልፈለገችም በጣም ደክሞት ስለነበር ትቷት ወደ መኝታው ይሄዳል።
·
በሁለተኛ ቀን ድጋሚ ያመሻል ሚስት ስትደውል ስልኩን ያነሳችው ሴት ነበረች «ሄሎ» ስትላት ስልኳን ተናዳ ትዘጋዋለች። ባል ሲገባ እሳት ለብሳ እሳት ጎርሳ ትጠብቀዋለች። ባሏም እንደገባ እንዲህ አለችዉ።
·
ሚስት፦ «እኔ ምንክ ነኝ ላንተ ?»
·
ባል፦ «ውድ ሚስቴ ነሻ።»
·
ሚስት፦ «ያቺስ»
·
ባል፦ «ከወደሁላው ዘወር ዘወር ይልና የቷ ?
·
ሚስት፦ «ስልኩን ያነሳችው ወይዘሮ»
·
ባል፦ «ስልኩን ለማውጣት እጁን ወደ ኪሱ ሲያስገባ ስልክ የለም። «ማሬ ስልኬ የለም፣» ይደነግጥና ማፈላለግ ይጀምራል።»
·
ሚስትም ሊዋሻት የፈለገ ስለመሰላት አላመነችው በቃ እንዲፈታት ትነግረዋለች። ባል ሊያረጋጋት ቢሞክርም አልቻለም። ባልም እሺ ይንጋና ነገ ወደ ቤተሰቦችሽ ትሄጃለሽ ብሎ ይለምናታል። በዚህ መልኩም እሱ መኝታ ቤት እሷ ደሞ የሳሎኑ ሶፋ ላይ ተለያይተዉ ተኙ።
·
በጠዋት የቤታቸው በር ይንኳኳል ሚስትም ከተኛችበት ሶፋ ላይ ነቅታ በሩን ስትከፍት አንድ አርጀት ያሉ ሴትዮ ከወጣት ሴት ልጃቸው ጋር ይመጡና ባሏ እንዳለ ይጠይቋታል። እሷም ትጠራዋለች ሴትዮዋም ስልኩን እርሳቸው ጋር እረስቶት እንደነበረ ነገረው ይሰጡትና በጣም ሲመርቁት ታያለች።
·
ሚስት፦ «ለምንድን ነው ብላ ስትጠይቅ ?»
·
የልጁ እናት፦ «ባልሽ በጣም ጥሩ ሰው ነው። ከቀኖች በፊት ለወንዱ ልጄ ደም ለግሶ የልጄን ሂወት ታደገልኝ።» የልጁ እናትም አስከትለዉ
«ትላንት ደግሞ ልጄን ሊጠይቅ መጥቶ ሳለቅስ አየኝ ለምን እንዳለቀስኩ ጠይቆኝ ለልጄ ከሆስፒታል የታዘዘለትን መድሀኒት መግዣ እንዳልነበረኝ ስነግረው በየ ሱቁ ሲፈልግ አምሽቶ ገዝቶ አመጣልኝ። እናም ሆስፒታል ዉስጥ ስልኩን እረስቶት ሄደ ስትደውይ ልጄ ነበረች ያነሳችው።»
·
ትላታለች ሚስትም በባሏ ታጋሽነትና ቸርነት ተገርማ ይቅርታ ትጠይቀዋለች።

ውድ እህቴ ከታሪኩ የምትማሪው ለነገሮች ኡዙር መስጠት እንዳለብሽ ነው። ባልሽ ላንቺ ታመኝ መሆኑን ልብሽን አሳምኝው። በትንሽ ነገር የአላህን ስጦታና የቤትሽን ጣፋጭ ደስታ ምድራዊ ጀነትሽን በቀላሉ አታበላሺዉ። እሱ ያንቺ ደስታ ነው የሚያስደስተው ግን የተቸገሩትንም መርዳት እንዳለበት አትርሺ።
·
ሁል ጊዜ ቤትሽን አስታዉሺ ላንቺ ብቻ ሳይሆን ለመላዉ ቤተሰብሽ ለአላህም ብለሽ።

:::::::ቴሌግራማችን::::::::

@lemuslimuaehte
166 viewsSofi@, 03:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 19:36:19 በሴት ልጅ መንገድ ላይ እሾህ አታስቀምጥ! እህትህ በዛ መንገድ ላይ ባዶ እግሯን ትመጣ ይሆናልና።

እያሰባችሁ!!!!!
@DinisNesiha
116 views. ...., 16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 13:33:50 አብሽር ይደረሳል



ከስጋህ ልቀህ ለነብስህ እደር፣ ወትሮውንም ብሂሉ " ስጋ ባዳ ነው " አይደል የሚለው ?
በውስጥህ ከተጧጧፈው የሞት ሽረት ትንቅንቅ፣ የሞራል ልዕልናህን ከፍ ለሚያደርግልህ፣ ውሎ አድሮም ዋጋ ለማያስከፍልህ ሀሳብ አድላ። ጭላጭ ስሜትን ከማነፍነፍ ተቆጥበህ፣ እንደባህር ሰርጎ ፣እንደተራራ ለሚፀና እሴት ግንባታ ታትር
ወደ ግብህ ለመድረስ በምታደርገው ግስጋሴ ፣ ትዕግስት እጅግ ጉልህ ሚናን ይጫወታል፣ በመታገስህ ውስጥ ያለው መራር ጣዕም፣ ቀጥሎ የሚመጣውን ጣፋጩን የድል ጣዕም አብሳሪ ነው።
አይዞህ በርታ
አይዞህ ፅና
አይዞህ ታገስ
ምንም ቢያደክም፣ የቱንም ያህል ቢሰለች፣ እመነኝ አስካልቆምክ ድረስ መድረስህ አይቀሬ ነው ።

“ታገስም፣ መታገስህም በአላህ እገዛ እንጂ በሌላ አይደለም ” ኢስራእ (17)
155 viewsSofi@, 10:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 08:03:36 የዝነቱ ነብይ
በአንድ ወቅት ነብዩ #ﷺ ቢላል ኢብኑ ረባህን ከኃላው በፍቅር ስሜት አይኑን በመሸፈን እቅፍ አድርገው ይይዙትና ድምፃቸውን ቀይረው..."እኔ ማን ነኝ"?
ቢላል (ረ.ዐ) :- ዑመር (ረ.ዐ) ነህ?
ነብዩ #ﷺ :- አይደለሁም
ቢላል (ረ.ዐ) :- አቡብክር (ረ.ዐ) መሆን አለብህ?
ነብዩ #ﷺ :- አሁንም ተሳስተሃል
ቢላል (ረ.ዐ) :- በቃ ዑስማን (ረ.ዐ) ነህ?
ነብዩ #ﷺ :- አላወቅከኝም
ቢላል (ረ.ዐ) :- ዓልይ (ረ.ዐ) ነህ ማለት ነው... እያለ
ያቀፈውን ሰው ማንነት ሲጠይቅ ይቆያል። ከዚያም
ረሱል #ﷺ ለቀቅ አደረጉትና ከፊት ለፊቱ በመምጣት "ቢላል ሆይ! እውነት እኔ መሆኔን አላወቅክም ነበር እንዴ"? ሲሉ ጠየቁት ቢላልም "የአላህ መልእክተኛ ሆይ!" በደንብ አውቄዎታለሁኝ ነገር ግን ለረጂም ጊዜ እንድታቅፉኝ ስለፈለኩኝ ነው ሲል መለሰላቸው።
ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙ አለይከ ያ ረሱሊላህ
ሳኒ & መሀመድ
https://t.me/lemuslimuaehte
179 viewsSofi@, 05:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 13:08:42 ዒማሙ አህመድ መሆን ካቃተህ
አቡል ኸይሰም ሁን

የታላቁ ዒማም አህመድ ዒብኑ ኸንበል ልጅ የሆነው አብደሏህ እንዲህ ሲል ይተርካል;

አባቴ ብዙ ጊዜ "አላህ ሆይ ለአቡ ኸይሰም ማረው, ለአቡል ኸይሰም ዕዘንለት" ሲል እሰማው ነበር።

አባቴ ሆይ አቡል ኸይሰም ማን ነው ብዬ ጠየቅኩት

"ከገጠሬዎች የሆነ አንድ ሰው ነው ፊቱን ራሱ አይቼው አላቅም።
ግን እነዝያ ያለፉት በሆኑ ስገረፍባቸው በነበሩት ሌሊቶች ውስጥ አንድ ቀን መግረፊያ ክፍል አስገብተው አስቀመጡኝ ሳለሁ; የሆነ ሰው ጀርባዬን መታ አረገኝና => {አህመድ ዒብኑ ኸንበል አንተ ነህን } አለኝ
አዎን አልኩት
=> {ታቀኛለህን }ሲለኝ
አላቅህም አልኩት

{እኔ አቡል ኸይሰም የተባልኩ የገጠር ሰው ነኝ, ኸምር እጠጣለሁ, የሰው ንብረትም ዕቀማለሁ, በዚህ ድርጊቴ መንግስት ፊት ቀርቤ አስራ ስምንት ሺህ ግርፋት በተለያዩ ጊዜያት ተገርፌያለሁ።
ይህ ሁሉ ስገረፍ ግን በሸይጣን መንገድ ላይ ሆኜም እችለው ነበር። አህመድ ሆይ አንተ ግን በአላህ መንገድ ላይ ነህና ሰብር አድርግ አለኝ።

ከዝያ በኋላ አስረው ሲገርፉኝ አንዲትን ግርፋት ባረፈችብኝ ቁጥር የአቡል ኸይሰም ንግግር ትዝ ይለኝና በውስጤ
{አህመድ ሆይ በአላህ መንገድ ላይ ነህና ሰብር አድርግ } እል ነበርኩ

አህመድ ዒብኑ ኸንበል መሆን ካቃተህ አቡል ኸይሰም ሁን

ምንም እንኳ ውድቅ የሆነ ነገር ላይ የተዘፈቅክ ብትሆንም የዕውነት ባልተቤቶችን ውደዳቸው

ምንም እንኳ በወንጀል የሰመጥክ ብትሆንም ደጋጎችን ውደዳቸው

ይ ላ ሉን share
┏━ ━━━━ ━┓
@DinisNesiha
┗━ ━━━━ ━┛
174 views. ...., 10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 11:53:24 እናትህን

1. ድምፅህን ከድምጿ በላይ ከፍ አታድርግ።
..
2. አጉል ክርክር አትከራከራት።
..
3. እሷ ሣትጨርስ አትናገር።
..
4. በስሟ አትጥራት።
..
5. እንቅልፏን ሣትጨርስ አትቀስቅሣት።
..
6. ለምክንያት ካልሆነ በስተቀር ከፊ ለፊትዎ አትቅደም።
..
7. ጠርታ ሳትጨርስ "አቤት" በላት።
..
8. ከቤት ወጥተህ አትዘግይባት።
..
9. በእይታህ አታፍጥባት።
..
10. በንግግርህ አታጋፍጣት።
..
11. በቁጣዋ አትቆጣ።
..
12. በንግግሯ አትቀልድ።
..
13. መላና ሀሣቧን አታናንቅ።
..
14. ሲጨንቃት አማክራት።
..
15. ሲቸግራት ቅረባትና እርዳት።
..
16. ስትታመም አስክማት።
..
17. ስትታረዝ አልብሣት።
..
18. ጉዳይዋን ሁሉ ጉዳዬ በል።
..
19. እቅድ ሀሣቧን ተካፈላት።
..
20. ካስከፋሀት ቶሎ ይቅርታ ጠይቃት።
..
21. ከእርግማኗ ተጠንቀቅ።
..
22. እሷን ከማስከፋት ፍፅም ራቅ።
..
23. ቀስ ብለ አስረዳት።
..
24. በሚገባት ሁኔታና ቋንቋ አስረዳት።
..
25. ለምርቃቷ ተሽቀዳደም።
..
26. ዓላማህን አትደብቃት።
..
27. እሷ ሳትቀመጥ አትቀመት

@lemuslimuaehte
238 viewsSofi@, 08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 12:14:39 አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ ውዶቼ ሪያዱ ሷሊሂን ደርስ ተጀመረ እንዳያመልጣችሁ በኡስታዝ ሙሀመድ ሲራጅ ሙሀመድ ኑር ወላሂ ውሸት አይደለም ኢልምን ከኡስታዞቻችን join
242 views. ...., 09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 11:27:47 ⇛ "ቆመሽ ቀረሽ!" እያሉ ሰዎች በምላሳቸው ልብሽን የሚያደሙት ከሆነ…< ለትዳር ለምን ዘገየሽ? >እያሉ የሚያደክሙሽ ከሆነ…

☞«በትዕግስት የጌታዬን እዝነት እጠብቃለሁ።» በያቸው!!…አወ!አላህ ትዳርሽን ያዘገየው እንደ ሉጥ ሚስት ከመሆን ሊጠብቅሽ፣ ድንበር ያለፈ ቢገጥምሽ እንደ አሲያ ሊየጠነክርሽ እንደሆነ አስቢ። የጌታሽ ጥበብ ረቂቅ ነው። አንዳንዴ የፈጠኑት በዘገዩት ይቀናሉ። በመልካም ስራ ታገሽ የታጋሾች ምንዳ ያማረ ነው። ምን ይታወቃል አላህ ከመልካሙ ጋር ሊያጣምርሽ አስቦ የሆናል!
‏«ﺭﺏّ ﺇﻧﻲ ﻟﻤﺎ ﺃﻧﺰﻟﺖّ ﺇﻟﻲّ ﻣﻦ ﺧﻴﺮ ﻓﻘﻴﺮ‏» ‏
http://T.me/HijabNewWebta
128 viewsخولة محمد, 08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 07:12:12 ከአሏህ ቀጥሎ ለራሴ ያለሁት እኔ ነኝ በይ
ያኔ አቅምሽን መጠቀም ትጀምሪያለሽ የተዘጉ የመሰሉሽ መንገዶች ሁሉ ይከፈታሉ ኢንሽ አላህ ለሰዉ ልጅ በላጭ
አልተሰጠዉም ሶብረ//ትእግስት ቢሆን እጅ  አላማሽ ትልቅ
ሲሆን ፈተናወች ይበዛሉ አንች ግን በሶብር ተራመጅ ቢዘገይም አሰብሽበት ትደርሻለሽ ትዕግስተኛ ሰው ሁሌም
አሸናፊ ነው   ሁልጊዜም መልካም ስነ ምግባር  ተለባሽ !
277 viewsSofi@, 04:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 19:49:08 አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ ውድ የቻናላችን ተከታታዮች እንደሚታወቀው የሪያዱ አሷሊሂን ደርስ ተጀምሩ ነበር እና እሱን እንቀጥል ወይስ ኪታቡ ተውሂድ እንጀምር ሀሳባችሁን አሳውቁን ባሰከላሁ ፊክ

ሪያድ
ተውሂድ
71 views. ...., 16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ