Get Mystery Box with random crypto!

School of ጮራ

የቴሌግራም ቻናል አርማ millionsankara — School of ጮራ S
የቴሌግራም ቻናል አርማ millionsankara — School of ጮራ
የሰርጥ አድራሻ: @millionsankara
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.03K
የሰርጥ መግለጫ

Learning Corners
a special learning activity for primary, Secondary and Preparatory pupils which strongly promotes Independence and Love of Learning.
🦋🦋
#Schoolofጮራ

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-07 09:44:14
የዘንድሮ 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 30/2015 ጀምሮ ይሰጣል።

የ2014 የትምህርት ዘመን ብሔራዊ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና ከመስከረም 30/2015 ዓ/ም ጀምሮ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጥ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

@millionsankara
267 viewsedited  06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 11:34:11 ራሴን በላሁት
-----
ገብቼ ሱባዔ
ለብቻ ጉባዔ
ላያሌ ዓመታት
በእኔነት ማሳ
ተመላልሼበት
ወጥቼ ወርጄበት
አዝመራ ባጣበት
ራሴን በላሁት
እየመነዘርኩት

(ደበበ ሰይፉ፤ የብርሃን ፍቅር፣ ገጽ 32፣ 1992)
288 views08:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 15:09:42 ታሪክን ወደ ሁዋላና ወደፊት
(በእውቀቱ ስዩም)

ያልተበረዘውን የኢትዮጵያ ታሪክ የሚያነብ ሰው ፥ መጀመርያ የሚመጣለት ስሜት “ wtf ? ምን ጉድ ነው ?” የሚል ነው ፤ ለምሳሌ ነገስታት አንድ ልማድ ነበራቸው ፤ልክ ዙፋን ላይ ሲወጡ ልጆቻቸውን እና ወንድሞቻቸውን ሰብስበው ከመዲናቸው ራቅ ያለ ማጎርያ ቦታ ያስቀምጧቸዋል፤ የማጎርያው መልክአምድር ለማምለጥ አይመችም፤ ከዚያም አልፎ፤ በንቁና አስፈሪ ዘበኞች ይጠበቃል፤ በአክሱም ዘመን ደብረዳሞ የልኡላን ማጎርያ ሆኖ አገልግሏል፤ የሸዋ ነገስታት በተራቸው ሲገዙ፤ ለዚህ ተግባር የመረጡት ቦታ፥ ወሎ ዛሬ ግሼን ማርያም የምትገኝበትን አምባ ነበር፤ የጎንደር ነገስታት በበኩላቸው ዘመዶቻቸውን “ወህኒ” ወደ ተባለ ስፍራ ማጋዝ ጀመሩ፤ ወህኒቤት የሚለውን ቃል የወረስነው ከዚህ ስፍራ ነው ፤ ወህኒ በመሰረቱ የፖለቲካ እስር ቤት ሲሆን ፥የመጀመርያው የፖለቲካ ወንጀል ከንጉስ መወለድ ነበር፤

ንጉሱ ድንገት ወራሹን ሳያሳውቅ በጦር ሜዳ ይገደላል እንበል፥ አንዱ የቤተመንግስት መኮንን ብድግ ይልና አንዱን ልኡል ከማጎርያ ቤት አውርዶ ዙፋን ላይ ያወጣዋል፤ ሌላው የጦር አዝማች ደግሞ የኔን ምርጫ ካላነገስኩ ሞቼ እገኛለሁ ብሎ ይነሳል፤ ባንጋሾች መካከል የሚደረገው ፉክክር መዲናይቱን ባንዴ ወደ ፍርስራሽ እና ያስከሬን ክምር ይቀይራታል::

የቀድሞ ሰዎች እንዲህ አይነቱን ብሄራዊ አደጋ ለመቀነስ የፈጠሩት “ዘዴ “ የንጉስን ሞት መሰወር ነበር ፤ የንጉስ ሞት ቀርቶ ህመሙ እንኳ ለህዘብ ይፋ አይደረግም፤ በዘመነ መሳፍነት ጊዜ ፥ የየጁው ራስ አሊ ሲሞት ፤ አንድ አሳባቂ ( የዘመኑ ፓፓራዚ) ወሬውን አሾለከው፤ ወድያው የረጋው አገር መላወስ ጀመረ፤ ጉዳዩ ያሳሰባት አንዲት አልቃሽ እንዲህ ብላ ገጠመች፥

“ እሻ እሻ ነው እንጂ የእስራኤልን ሞት
እንዲያልቅሰው አሊን ለምን ቀበሩት “

“ እሻ እሻ “ ማለት ዝም በሉ ጸጥ በሉ ማለት ነው ፤ በዘመኑ የንጉስ ወገን ነን የሚሉ ሰዎች ዘራቸውን ከሰለሞን ስለሚመዝዙ “ እስራኤል “ በሚል የወል ስም ይታወቃሉ፤
በግጥሙ መስመር ላይ ያለው ህብረቃል “ እንዲያልቅሰው “ የሚል ነው፤ ሰሙ “ እንዲህ አልቅሰው “ ሲሆን ወርቁ “ ሰው እንዲተላለቅ” የሚል ትርጉም አለው ፤

ባጭሩ አልቃሺቱ፥
“ ህዘብ እንዳይተላለቅ
የንጉስ ሞት ይደበቅ “ ማለት ነው የፈለገችው ፤

ከጥንት እስከዛሬ አገረ -መንግስታችን የሚቆመው ባንድ ሰው ትከሻ ላይ ነው ፤ መሪ ሲታመም አገር ይታመማል፤ መሪ ሲሞት አገር በጥቂቱ ይሞታል፤ ይህንን መለወጥ የሚቻለው እንዴት ነው? የማይሞቱ ተቋሞችን በመገንባት ፤ የማይታመሙ ህጎችን በመመስረት? ወይስ ሌላ መላ አለ?
394 views12:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 07:55:36
#ትምህርት_ሚኒስቴር

የ2014 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በ12 ኮድ (በጥያቄ አቀማመጥ ስብጥር) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው።

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከዚህ በፊት እንደነበረው በ4 ኮድ (4 የተለያዩ ፈተናዎች/በጥያቄ አቀማመጥ) ሳይሆን እስከ 12 እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ይህ የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ከሚሰሩት ስራዎች መካከል አንዱ መሆኑን የሚገልፁት ፕ/ር ብርሃኑ ጎን ለጎን ያሉ ተማሪዎች እርስ በእርስ የሚፈተኑት ፈተና የጥያቄው ዝርዝር (order) በፍፁም የተገናኘ እንዳይሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ፈተናው በዩኒቨርሲቲዎችና በፌዴራል ተቋማት እንደሚሰጥም ገልፀዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢፕድ የሰጡት ቃል፦

" ...የክልል ባለሟሎች፣ የክልል ኃላፊዎችን ከፈተና ጉዳይ ጋር እንለያቸው ፤ ፈተናው እራሱ የፌዴራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ስለሆነ በፌዴራል ተቋማት ውስጥ ብቻ እንስጥ ብለን አሁን በሙሉ ተማሪዎቹን አጓጉዘን ቢቻል ሁሉንም ከክልላቸው ውጭ በሆኑ ክልሎች ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እና የፌዴራል ተቋማት ውስጥ ለመስጠት ነው እየተዘጋጀን ያለነው።

ያ የሚያደርገው ሁለት ነገር ነው። አንደኛ በመንገድ ላይ ሊኖር የሚችለውን የመሰረቅ አደጋ ይቀንሰዋል። ሁለተኛ ክፍል ውስጥ ከተገባ በኃላ ለመስረቅ የሚቻልበትን አደጋ ይቀንሰዋል።

ከዛም በላይ ፈተናዎቹን በማዘጋጀት ደረጃ በፊት በ4 የተለያዩ ፈተናዎች ነበር የምናዘጋጀው እስከ 12 አድርገን Completely scrambled እንዲሆኑና ማንም ጎኑ ያለው ተማሪ የሚፈተነው ፈተና አንተ ከምትፈተነው ፈተና order ጋር በፍፁም ያልተገናኘ እንዲሆን አድርገን እየሰራን ነው።

ይሄ በጣም በብዙ ደረጃ የፈተና ስርቆትን ይቀንሰዋል ብለን ነው ተስፋ የምናደርገው። "

@tikvahethiopia
388 views04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 07:42:47
#ያመኛል_ብለህ_ማሰብህ_ያሳምምሀል

ኬሞቴራፒ ይባላል- ለካንሰር በሽተኞች የሚሰጥ ህክምና ነው። ህክምናው እጅግ ህመም ፈጣሪ ሲሆን ማጥወልወል፣ ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ ዋነኛ ከህክምናው በኋላ የሚፈጠሩ ህመሞች ናቸው።

በሮቺስተር በተሰራው የካንሰር ጥናት መሰረት፣ ኬሞቴራፒውን ከሚወስዱት ታማሚዎች ውስጥ 40% የሚሆኑት የሚያጥወለውላቸው ህክምናውን ከወሰዱ በኋላ እንደሚያማቸው በሃኪሙ ስለተነገራቸው ብቻ ነው።

እንዲያውም ኬሞቴራፒውን እየተመላለሱ ከሚታከሙት መሃል ሃያ ዘጠኝ ፐርሰንቱ የኬሞቴራፒውን ህክምና የሚያስታውሳቸው ነገር ሲመለከቱ ወይም ሲያሸቱ ሽቅብ ወደ ላይ ይላቸዋል። ወደ አስራአንድ ፐርሰንት ገደማ የሚሆኑት ደግሞ ገና ህክምናውን ለመከታተል ሆስፒታል ከመድረሳቸው በፊት በመንገድ ላይ ሳሉ ያቅለሸልሻቸዋል።

እንዴት ሰዎች ገና ኬሞቴራፒውን ሳይወስዱ አመማቸው? ያመናል ብለው ማሰባቸውስ ይሆን ከህክምናው በኋላ እንዲታመሙ ያደረጋቸው? አርባ ፐርሰንቱ ታካሚዎችስ ህክምናው ህመም እንደሚፈጥርባቸው ባያምኑ፣ ያለምንም ስቃይ ወደ ቤታቸው ይመለሱ ነበር? መልካም ማሰብ ብቻውንስ ጤነኛ ያደርገናል?

በጠራራ ጸሃይ ዝናብ ይዘንባል ብለህ ዣንጥላ ይዘህ ከምትወጣ፣ ደመና ባጠላበት ሰማይ ስር አይዘንብም ብለህ ወጥተህ ቢዘንብ እንኳን በዝናቡ ውስጥ ደንስ።

#ጭንቅላትህን_አጽዳ መጽሐፍ

*
ቤተሰብ ይሁኑ
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/

Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
566 viewsedited  04:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 16:21:14
#ማራ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

#ሙሉ_በሙሉ_እውነተኛ_ታሪክ

የሞት ፍርድ የተፈረደባት አንዲት እንስት ይቅርታ ጠይቂና የሞት ፍርዱ ይነሳልሽ ብትባል እንቢ አሻፈረኝ ትላለች፡፡

ምሕረትን እንዳትቀበል ያደረጋት፣ ሕይወቷን ያስመረረውና የሞት ጽዋውን ያሰኛት ምክንያት ምን ይሆን?

የሴተኛ አዳሪዎች ንግስት፣ የልኡላን ቅምጥ የሆነችው እንስት በሴቶች የሚደረጉ አስገራሚ አብዮቶች ምልክት ተብላ ተሞግሳለች፡፡ ሙሉ በሙሉ እውነተኛ ታሪክ የሆነው #ማራ መጽሐፍ እነሆ በገበያ ላይ ውሏል፡፡


“ከእስር ቤት የምትወጪበት አንድ ተስፋ ተገኝቷል፡፡ ለፕሬዚዳንቱ የይቅርታ መልዕክት ፅፈሽ ይቅርታ እንዲደረግልሽና ሁለተኛ ወንጀል ላለመስራት ቃል የምትገቢ ከሆነ ከእስር ቤት እንደምትወጪ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡”

“ይቅርታ እኔ ነፃ መሆን አልፈልግም፡፡ ለሰራሁት ወንጀል ደግሞ ይቅርታ መጠየቅ አልፈልግም፡፡ በዚያ ላይ እናንተ ወንጀል ብላችሁ የምትጠሩት ወንጀል አይደለም” አልኩት፡፡ “ከዚህ ወጥቼ አንተ እንደምትለው እንደገና መኖር ብጀምር መግደሌን አላቆምም፡፡ ስለዚህ የይቅርታ ደብዳቤ ለፕሬዚዳንቱ መላክ አያስፈልግም፡፡ እኔ በመኖርም፣ በመሞት… በሁለቱም አሸናፊ ነኝ፡፡”

“አንቺ ወንጀለኛ ነሽ!”

“አይደለሁም! እናንተ ሁላችሁም ወንጀለኞች ናችሁ፡፡ አባቶች፣ አጎቶች፣ ባሎች፣ የሴተኛ አዳሪ ደንበኞች፣ ሁላችሁም ወንዶች! አባቴ፣ አጎቴ፣ ባሌ… ሁላችሁም ሴተኛ አዳሪ ሆኜ እንዳድግ አስተምራችሁኝ አልፋችኋልና ወንጀለኞች ናችሁ!!!”
#ከመጽሐፉ_የተወሰደ

#ማራ መጽሐፍ
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል፡፡
*

https://t.me/teklu_tilahun
822 viewsedited  13:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 12:18:33
522 views09:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 07:41:13
#የህይወት_ወርቃማ_ህጎች_2

#ያለ_ፍርሃት_በአዎንታዊነት_ተንቀሳቀስ
የሆነ ነገር ውስጥ እንደገባህ በተሰማህ ጊዜ ሁሉ… ተረጋጋ፣ አስብ፣ እቅድ አውጣና ያለ ፍርሃት በአዎንታዊነት ተንቀሳቀስ። የፍርሃት ወጥመድ ውስጥ መቆየትና አሉታዊ ነገሮችን ማሰብ ብቻ መፍትሄ አይሆንም፨ ስለዚህ, በእያንዳንዱ አሉታዊ ሁኔታ ውስጥ አዎንታዊ ጎን መፈለግ ተማር፨

#በረከቶችህን_ቁጠር_መልካም_አድርግ
በውጤቱ ላይ ሳታተኩር መልካም መስራትህን ቀጥል፤ ሁልጊዜም የዘራነውን የምናጭድ በመሆኑ በተቻለ መጠን መልካም ነገሮችን ስራ፨ በተጨማሪም ያለፈው ጊዜ ታሪክ ነው፣ መጪው ጊዜ ምስጢር ነው፣ ዛሬ ደግሞ ስጦታ ነው። ስለዚህ ዛሬ ላይ ትኩረት አድርግ፨

#ፈገግ_ማለትህን_ቀጥል
አንድ ቀላል ፈገግታ የአንድን ሰው መጥፎ ቀን ወደ ጥሩ ቀን ሊለውጠው ይችላል። ስለዚህ፣ ፈገግ ማለትህን ቀጥል ይህም የአንተን ግንዛቤ ይለውጣል፨

#ሲያስፈልግ_ብቻ_ይቅርታ_ጠይቅ
አሁን አሁን <ይቅርታ> እና <አዝናለሁ> የሚሉት ቃላት በሚጠቀሙባቸው በአብዛኛው ሰዎች ከቃላት ባለፈ ብዙም ትርጉም የላቸውም፨ ይቅርታ መጠየቅ መልካም ቢሆንም፥ ከመጠን በላይ ይቅርታ መጠየቅ ግን ሰዎች የሚፈለገውን አክብሮት እንዳይሰጡህ ያደርጋል፨ ስለዚህ ይቅርታ ስትጠይቅ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ብቻ ይሁን።

#ወርቃማ_ሕጎች መጽሓፍ https://www.facebook.com/booklandbook/
610 viewsedited  04:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 08:04:23
#አባዬ_ጎበዝ_ነህ!

አንድ እውነተኛ ታሪክ ላጫውትህ። ከአመታት በፊት ፓሪስ ውስጥ በሚገኝ የኦፔራ አዳራሽ ውስጥ ሙዚቃውን ሊያቀርብ አንድ ታዋቂ ዘፋኝ ስምምነትን ፈጸመ። እሱ እንደሚመጣ የሰሙ አድናቂዎቹ የመግቢያ ትኬቶችን ተጋፍተው ገዙ። ሙዚቃው በሚቀርብበት እለትም፤ የመድረክ አስተናባሪው ንግግር ማድረግ ጀመረ -

"ክቡራት እና ክቡራን፤ በትዕግስት ስለጠበቃችሁን እናመሰግናለን፤ ሆኖም ለዛሬ ቀጠሮ የተያዘለት ሙዚቀኛ በህመም ምክንያት ሊገኝ አልቻለም። ነገር ግን በእርሱ ምትክ ሌላ ሙዚቀኛ ፕሮግራሙን የሚያስቀጥለው ይሆናል"

ታዳሚዎቹ አጉረመረሙ፤ ይህንን ጠብቀው አልነበረም የመጡት።

ተጠባባቂ የተባለው ሙዚቀኛ ሙዚቃውን አቀረበ። ሲጨርስም፤ አዳራሹ ምቾት በማይሰጥ ሰጥታ ተዋጠ። በመሃል አንድ ህጻን ልጅ ከወንበሩ ተነሳና -

"አባዬ፤ ጎበዝ ነህ!" የሚል ድምጽን አሰማ። አዳራሹን የሞሉት ታዳሚዎች ይህንን ሲሰሙ እንባ እያነቃቸው ማጨብጨብ ጀመሩ...

አንዳንዴ በህይወታችን ውስጥ "ጎበዝ ነህ፤ በርታ!" ብለው የሚገፉን ሰዎች ያስፈልጉናል። የመጣህበትን መንገድ ባላውቀውም፤ ያለፍካቸው ብዙ ችግሮች እንቅፋቶች እና መከራዎች አሉና አይዞህ በርታ፤ ጎበዝ ልልህ እወዳለሁ።

አይዞህ በርታ!!!

#የሕይወት_መመሪያ መጽሐፍ

* https://www.facebook.com/booklandbook/

https://t.me/teklu_tilahun
568 viewsedited  05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 18:06:48
565 views15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ