Get Mystery Box with random crypto!

AHADU RADIO FM 94.3

የቴሌግራም ቻናል አርማ ahaduradio — AHADU RADIO FM 94.3 A
የቴሌግራም ቻናል አርማ ahaduradio — AHADU RADIO FM 94.3
የሰርጥ አድራሻ: @ahaduradio
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.23K
የሰርጥ መግለጫ

አሐዱ ራድዮ 94.3
Your source for top local and international news and analysis.
"Voice of Ethiopian"
የአሐዱ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ወቅታዊና እውነተኛ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-05-19 19:07:51
የሰሜኑ ጦርነት በሰላም ስምምነት ከተጠናቀቀ በኋላ መንግስት በአማራ ክልል ላይ የያዘው አቋም ከህግ አግባብ ውጪ መሆኑን ህብር ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታወቀ፡፡

እንደ ሃገር የሰሜኑ ክፍል ጦርነት በብዙ መልኩ ዋጋን ያስከፈለ መሆኑን አስታውሰው በህወሃት እና በፌደራል መንግስቱ መካከል በፕሪቶርያ የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተገቢ እና ትክክለኛ አማራጭ ነው ያሉት የህብር ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ኢንጂነር ይላቃል ጌትነት ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ከሰላም ስምምነቱ በኋላ መንግስት በተለየ መልኩ በአማራ ክልል ላይ የያዘው አቋም ህገ ወጥ ነው ያሉት ምክትል ሊቀመንበሩ የተለያዩ ምክንያቶችን እየሰጡ የክልሉን ዜጎች ማጉላላት እና ከህግ አግባብ ውጪ በሆኑ ድርጊቶች ማንገላታት በተደጋጋሚ እየተስተዋለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይህ ከመሆኑም ባለፈ ክልሉን የጦርነት ቀጠና ለማድረግ እየተሄደበት ያለው መንገድ አግባብ ባለመሆኑ ፓርቲያቸው ህግ እንዲከበር መንግስትን ይጠይቃል ብለዋል፡፡ ለሃገር ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ እና የዜጎች መብት መከብር መንግስት መወጣት ያለበት ሚና የላቀ ቢሆንም በዛ ልክ ግን እየሰራ አይደለም ያሉት ኢንጂነር ይልቃል ፓርቲያቸው በመንግስት በኩል የሚስተዋሉ ችግሮች በአፋጣኝ እልባት እንዲያገኙ አጽንኦት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል፡፡ ህብር ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሀገራዊ ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ በትላንትናው እለት ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
2.3K views16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 18:19:00
ወቅታዊ ይሁን ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የዲሞክራሲ ተቋማት የሚሰጡት ምክረ ሀሳብ ግንዛቤ ውስጥ ሳይገባ በተናጠል የሚሰጠው ውሳኔ ዜጎችን እየጎዳ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

አሃዱ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ፤የሰብዓዊ መብት ኮምሽን ሌሎችን ተቋማትን ጨምሮ በወቅታዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚሰጡት ምክረ ሀሳቦች ለምን አይተገበሩም ሲል የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋምን ጠይቋል፡፡ ምላሽ የሰጡት የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና እንባ ጠባቂ ዶክተር እንዳለ ሀይሌ ተቋማት የሚሰጡትን ምክረ ሀሳብ ወስዶ ተግባራዊ እንዲሆን አለመደረጉ የዲሞክራሲ ልምምድ አለመኖሩ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

ዲሞክራሲን ተግባራዊ እያደረግን ነው ካልን አሁን ያሉትን ችግሮች ተወያይቶ ስምምነት ላይ መድረስ ያስፍልጋል ያሉት ዶክተር እንዳለ የብሄር አስተሳሰብ እና መሰል ችግሮች መፍትሄ ሳያገኙ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የተናጠል ውሳኔዎች ማስተላለፍ ዜጎችን እየጎዳ ነው ብለዋል፡፡ ለዜጎች ሰብዓዊ መብት ጥሰት፤ለጦርነቱም ምክንያት ከሆኑት ነገሮች መካከል እየዳበረ የሚመጣ የዲሞክራሲ ስርዓት ባለመገንባቱ ነው ያሉት ዶክተር እንዳለ፤ አሁን ላይ በፍርድ ቤቶች የሚሰጡ ውሳኔዎች የህብረተሰቡን እምነት የሚሸረሽሩ በመሆናቸዉ ዋጋ እያስከፈለን ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ 
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
2.6K viewsedited  15:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 18:30:52
የአረብ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች የሶሪያን ወደ አረብ ሊግ መመለስ በመልካም መቀበላቸዉን አስታዉቀዋል፡፡

ሚንስትሮቹ ከሊጉ አመታዊ ስብሰባ ቀደም ብለው የሶሪያን መመለስ በመልካምነት መግለጻቸውንና በሱዳን የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ ማቅረባቸው ነው የተነገረው፡፡ በጂዳ የሚካሄደው አመታዊ ስብሰባ በጦርነት የደቀቀችው ሶሪያን መልሶ መገንባት ላይ እንደሚያተኩርና ሶሪያ ከአስራ ሁለት አመታት እገዳ በኋላ ወደ ሊጉ እንደምትመለስም ተዘግቧል፡፡

ሶሪያ ከሊጉ አባልነት የታገደችው በፈረንጆች 2011 በተካሄደው ህዝባዊ አመጽ የፕሬዝዳንት ባሺር አላሳድ መንግስት ያደረገውን ጭፍጨፋ ተከትሎ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ ከአመጹ በኋላም ሀገሪቱ ግማሽ ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች ወደ ሞቱበት የእርስበርስ ጦርነት እንዳመራች ተነግሯል፡፡

ዘገባው፡-የእስታር ትሪቡን ነው፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
3.2K views15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 18:00:32
ጋና የእንግሊዝ ሙዚየም የተሰረቁ ወርቆቼን መመለስ አለበት አለች፡፡

በጋና ዋና ከሚባሉ ጎሳዎች አንዱ የሆነው የሆነው የአሻንቴ ጎሳ መሪ የእንግሊዝ ሙዚየም የተሰረቁ ወርቆችን እንዲመልስ መጠየቃቸው ተዘግቧል፡፡
ቅርሶቹ በሚመለሱበት ሁኔታም የጎሳው መሪ ከሙዚየሙ ዳይሬክተር ጋር መነጋገራቸው ተነግሯል፡፡
እንዲመለሱ የተጠየቁት በፈረንጆቹ 1874 ከእንግሊዞች ጋር በነበረ ጦርነት ከአሻንቴ ቤተ መንግስት የተወሰዱ ቅርሶችንም ያጠቃልላል ነው የተባለው፡፡

በእንግሊዝ ወታደሮች የተወሰዱ ሁለት መቶ ያህል የወርቅ ቁሶች በሙዚየሙ ውስጥ እንደሚገኙ ተዘግቧል፡፡ የሙዚየሙ ቃል አቀባይ የሶሰተኛው አንግሎ አሻንቴ ጦርነት መጠናቀቅ አስመልክቶ የመቶ ሀምሳኛ እዩቤልዩ ሲከበር ከቅርሶቹ ስብስብ የተወሰኑትን በውሰት የሚሰጡበት ሁኔታዎች እየተጤኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ዘገባው፡-የየዘ ቮይስ ኒውስ ነው፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
3.0K views15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 17:30:37
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸረ ማሰቃየት ኮሚቴ ያወጣው ሪፖርት አዲስ አይደሉም ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ በአለም ዓቀፍ ደረጃ ካጸደቀቻቸው የሰብአዊ መብት ስምምነቶች መካከል አንዱ የሆነው እና በ1994 አጽድቃ አባል የሆነችበት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸረ ማሰቃየት ኮሚቴ በኢትዮጵያ ያለውን የታራሚዎች አያያዝ እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ ባሳለፍነው አርብ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ አሐዱ መግለጫው ዙሪያ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ኮሚሽነር ዶክተር አብዲ ጅብሪልን አነጋግሯል፡፡

ኮሚቴው አሳስቦኛል ያለው በኢትዮጵያ ግጭት ባለባቸው የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እና በማረሚያ ቤት ያለው ኢ-ሰብአዊ አያያዝ እነ እሱም ከዚህ በፊት በተለያየ ጊዜ ባወጧቸው ሪፖርቶች የተገለጹ ሲሆን፡፡ ለዚህም መንግስት አስፈላጊውን እርምጃ እወስዳለሁ ብሎ ወደ ስራ መግባቱን እና ተጠያቂዎችን ለፍርድ ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን አንስተው የኮሚቴው ሪፖርት አጽንኦት ለመስጠት እንጂ አዲስ ጉዳይ አይደለም ብለዋል፡፡
ኮሚቴው በስምምነቱ አባል የሆኑ ሃገራትን በሰብአዊ መብት አያያዝ ያስመዘገቡትን በጎ ውጤት እና ያጋጠሙ ችግሮችን የሚገልጽ እንጂ በፍርድ ቤት ደረጃ አከራክሮ አንዱን ጥፋተኛ ሌላውን ተጠቂ የሚያደርግ አይደለም ሲሉም ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
2.6K views14:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 17:01:04
በትግራይ ክልል በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1 ሺ 2 መቶ 31 ያልመከኑ ፈንጂዎች መገኘታቸው ተገለጸ፡፡
በሀገሪቱ በሰሜኑ ክፍል በነበረው ጦርነት ጉዳት ከደረሰባቸው ተቋማት አንዱ ትምህርት ቤቶች በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳሉ፡፡
ከሰላም ስምምነቱ በኃላ 1 ሺ 2 መቶ 18 ትምህርት ቤቶች የተከፈቱ ሲሆን 7 መቶ 22ቱ የሚሆኑት በደረሰባቸው ከባድ ጉዳት አገልግሎት አለመጀመራቸውን ለአሐዱ የተናገሩት የህጻናት አደን ድርጅት በኢትዮጵያ /ሴቭ ዘ ችልድረን/ የትግራይ ክልል አስተተባባሪ አቶ አታክልቲ ገብረ ዩሀንስ ናቸው፡፡
ተማሪዎች 3 ዓመት የትምህርት ገበታቸው ላይ አለመገኘታቸውን ያነሱት አስተባባሪው አሁን ላይ ለ39 ሺ መምህራን የ3 ወር ደሞዝ መከፈሉን ተናግረዋል፡፡
ትምህርት ቤቶችን ከስጋት ነጻ ለማድረግ እና የተማሪዎቹ ደህንነት እንዲጠበቅ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸውን እና ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ጋር በተሰራው ስራ በ1ሺ 544 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1 ሺ 2 መቶ 31 ያልመከኑ ፈንጂዎች መገኘታቸውን አንስተዋል፡፡
ድርጅቱ የተሸከርካሪ እና ሌሎች ድጋፎችን በማድረግ በጋራ በተሰራው ስራ ትምህርት ቤቶችን ከስጋት ነጻ ማድረግ እንደተቻለም ተናግረዋል፡፡ለ40ሺ ተማሪዎች በ59 ትምህርት ቤቶች ላይ የህጻናት አደን ድርጅት በኢትዮጵያ/ የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጉን አመላክተዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
2.5K views14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 15:47:26
የማኀበራዊ ጥበቃ አገልግሎቶችን የሚፈልጉ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ ቢሆንም አፈጻጸሙ ግን አነስተኛ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የማህበራዊ ጥበቃ ፕሮግራሞችን በተለያዩ የመንግስት እና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት የሚተገበሩ በመሆናቸዉ አቀናጅቶ ለመምራት እና አፈፃፀሙን ለማሳደግ ብሄራዊ የማህበራዊ ጥበቃ ፖሊሲ እና የማስፈፀሚያ ስትራቴጂ ተቀርፆ በመተግበር ላይ እንደሚገኝ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር አስታዉቋል፡፡ የማኀበራዊ ጥበቃ አገልግሎቶችን የሚፈልጉ ዜጎች ቁጥር በየጊዜው በሚከሰቱ ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሠራሽ ችግሮች ምክንያት እየጨመረ ቢሆንም የፖሊሲዉ አፈጻጸም ግን አነስተኛ መሆኑን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ተናግረዋል።

ፖሊሲውን እና የማስፈጸሚያ ስትራቴጂውን በሚገባ በመተግበር እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል ጠንካራ የማኀበራዊ ጥበቃ ሥርዓት መዘርጋት እንደሚገባ ገልፀዉ ለዚህም የሚመለከታቸው አካላት ርብርብ ወሳኝ እንደኾነ ገልፀዋል። አሁን ካለው ዓለማቀፋዊ እና ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታ አኳያ የማኀበራዊ ጥበቃ አገልግሎቶችን በማሳደግ ፤ሥርዓትን የመገንባት አስፈላጊነትና ጠቀሜታውን በማሳወቅ የተለያዩ አካላትን ግንዛቤ የማሳደግ ስራ እንደሚሰራ አክለዋል

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
3.0K views12:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 18:01:48
የአሜሪካው ማእከላዊ የደህንነት ኤጀንሲ CIA ለሩሲያውያን ያልተለመደ ጥሪ አቅርቧል፡፡
የስለላና የደህንነት ተቋሙ አንድ ተንቀሰቃሽ ምስል በቴሌግራም ለቅቋል፡፡

በምስሉም ላይ በሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላዲሚር ፑቲንና በአስተዳደራቸው የተከፋችሁና የተገፋችሁ ሩሲያውያን ወደ እኔ ኑ ሲል ጥሪ አቅርቧል፡፡
ባለስልጣናትን ጨምሮ በርካታ ሩሲያውያን በሀገራቸው መንግስት በደል እየደረሰባቸው ነው የሚለው CIA፤ ለውጥ ማምጣት ከፈለጋችሁ አስፈላጊ መረጃዎችን ብትሰጡኝ ትጠቀማላችሁ ሲል ነው ጥያቄውን ያቀረበው፡፡

ጥሪ የቀረበላቸው ሩሲያውያንም መረጃ ማቀበላቸውን ለለውጥ እንጂ እንደ ሀገር ክህደት እንዳይቆጥሩትም ነው የአሜሪካው ማዕከላዊ የደህንነት ኤጄንሲ ያበረታታው፡፡ ተንቀሳቃሽ ምስሉን በቴሌግራም መልቀቅ የተፈለገው ደግሞ በርካታ የሩሲያና የዩክሬን ከፍተኛ ባለስልጣናት የፖለቲካዊ ጉዳዮችን የሚያንሸራሽሩት በዚህ ማህበራዊ መገናኛ አማራጭ በመሆኑ ነው ሲል የዘገበው ዩሮ ኒውስ ነው፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
2.2K views15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 17:01:02
የአፍሪካ ሀገራት በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ሰላም እንዲወርድ ለማስቻል የልኡካን ቡድን ለአደራዳሪነት ሊልኩ መሆናቸው ተገለጸ፡፡

ስድስት የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችን የሚያካትት የልኡካን ቡድን በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል ያለውን ወጥረት በማርገብ ሰለም እንዲወርድ ለማስቻል እየተንቅሳቀሱ እንደሚገኙ የደቡብ አፍረካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማ ፎሳ አስታውቀዋል፡፡
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎደሜር ዘለንስኪ የልኡካን ቡድኖቹን በየመዲናዎቻቸው ለመቀበል መስማማታቸውም ተገልጿል፡፡
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ከሁለቱም ሀገራት ፕሬዝዳንቶች ጋር ባሳለፍነው የእረፍት ቀናት ውስጥ ረጅም የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን አያይዘው ይፋአድርገዋል፡፡

ሲሪል ራማ ፎሳ ይህ ለሰላም የማደራደር እና የማስማማት ጽንሰ ሀሳብ ከዛምቢያ፣ ሴኔጋል፣ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ፣ ዩጋንዳ፣ ግብጽ እና ደቡብ አፍሪካ የመጣ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡
በዚህ የሰላም ድርድር ሂደት ላይ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው ረዘም ያለ ውይይት እንደሚደረግ እና የሁለቱም ሀገራት መሪዎች ጥያቄውን በመልካም መቀበላቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ዘገበው፡- የኔሽን ኒውስ ነው፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
2.2K views14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 16:02:04
ኢትዮጵያውያን ለውጪ አገራት የስራ ስምሪት በሚጓዙባቸው አገራት ከሚገኙ የሰራተኛ ማህበራት በኩል የህግ ከለላ እንዲያገኙ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ለውጪ አገር የስራ ስምሪት በዋናነት የአረብ አገራትን ተመራጭ እንደሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በእነዚህ አገራት በስራ ላይ ለሚደርስባቸው በደሎች እና መሰል ጉዳዮች የህግ ከለላ እንዲያገኙ የሚያስችሉ ስምምነቶች መደረጋቸውን የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ አስታውቀዋል፡፡ ብዙ ኢትዮጵያውያን ከሚገኙባቸው የአረብ ሀገራት መካከል ሊባኖስ እና ኩዌይት ተጠቃሽ ሲሆኑ በእነዚህ አገራት የሚገኙ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽኖች ለኢትዮጵያውያን ሰራተኞችም የህግ ከለላ እንዲሰጡ የሚያስችሉ ስምምነቶችን በመፈራረም በጋራ እየሰሩ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም ሌላኛዎቹ የኢትዮጵያውያን መዳረሻ ከሆኑት ኳታር ፣ ባህሬን እና ኦማን የሰራተኛ ማህበራት ጋር በመነጋገር ላይ የሚገኙ ሲሆን በቅርብ ጊዜ ውስጥ ስምምነት እንደሚፈራረሙ እና የዜጎችን ደህንነት የማስጠበቅ ስራን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም በሳውዲ አረቢያም መሰል ስምምነቶችን ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት የተደረገ ቢሆንም በአገሪቱ ምንም አይነት የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ባለመኖሩ ምክንያት እስካሁን ውጤታማ ሊሆን እንዳልቻለ አመላክተዋል::

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
2.2K views13:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ