Get Mystery Box with random crypto!

የአረብ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች የሶሪያን ወደ አረብ ሊግ መመለስ በመልካም መቀበላቸዉን አስታዉቀዋል | AHADU RADIO FM 94.3

የአረብ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች የሶሪያን ወደ አረብ ሊግ መመለስ በመልካም መቀበላቸዉን አስታዉቀዋል፡፡

ሚንስትሮቹ ከሊጉ አመታዊ ስብሰባ ቀደም ብለው የሶሪያን መመለስ በመልካምነት መግለጻቸውንና በሱዳን የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ ማቅረባቸው ነው የተነገረው፡፡ በጂዳ የሚካሄደው አመታዊ ስብሰባ በጦርነት የደቀቀችው ሶሪያን መልሶ መገንባት ላይ እንደሚያተኩርና ሶሪያ ከአስራ ሁለት አመታት እገዳ በኋላ ወደ ሊጉ እንደምትመለስም ተዘግቧል፡፡

ሶሪያ ከሊጉ አባልነት የታገደችው በፈረንጆች 2011 በተካሄደው ህዝባዊ አመጽ የፕሬዝዳንት ባሺር አላሳድ መንግስት ያደረገውን ጭፍጨፋ ተከትሎ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ ከአመጹ በኋላም ሀገሪቱ ግማሽ ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች ወደ ሞቱበት የእርስበርስ ጦርነት እንዳመራች ተነግሯል፡፡

ዘገባው፡-የእስታር ትሪቡን ነው፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24