Get Mystery Box with random crypto!

ወቅታዊ ይሁን ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የዲሞክራሲ ተቋማት የሚሰጡት ምክረ ሀሳብ ግንዛቤ ውስጥ ሳይገባ | AHADU RADIO FM 94.3

ወቅታዊ ይሁን ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የዲሞክራሲ ተቋማት የሚሰጡት ምክረ ሀሳብ ግንዛቤ ውስጥ ሳይገባ በተናጠል የሚሰጠው ውሳኔ ዜጎችን እየጎዳ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

አሃዱ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ፤የሰብዓዊ መብት ኮምሽን ሌሎችን ተቋማትን ጨምሮ በወቅታዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚሰጡት ምክረ ሀሳቦች ለምን አይተገበሩም ሲል የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋምን ጠይቋል፡፡ ምላሽ የሰጡት የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና እንባ ጠባቂ ዶክተር እንዳለ ሀይሌ ተቋማት የሚሰጡትን ምክረ ሀሳብ ወስዶ ተግባራዊ እንዲሆን አለመደረጉ የዲሞክራሲ ልምምድ አለመኖሩ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

ዲሞክራሲን ተግባራዊ እያደረግን ነው ካልን አሁን ያሉትን ችግሮች ተወያይቶ ስምምነት ላይ መድረስ ያስፍልጋል ያሉት ዶክተር እንዳለ የብሄር አስተሳሰብ እና መሰል ችግሮች መፍትሄ ሳያገኙ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የተናጠል ውሳኔዎች ማስተላለፍ ዜጎችን እየጎዳ ነው ብለዋል፡፡ ለዜጎች ሰብዓዊ መብት ጥሰት፤ለጦርነቱም ምክንያት ከሆኑት ነገሮች መካከል እየዳበረ የሚመጣ የዲሞክራሲ ስርዓት ባለመገንባቱ ነው ያሉት ዶክተር እንዳለ፤ አሁን ላይ በፍርድ ቤቶች የሚሰጡ ውሳኔዎች የህብረተሰቡን እምነት የሚሸረሽሩ በመሆናቸዉ ዋጋ እያስከፈለን ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ 
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24