Get Mystery Box with random crypto!

የሰሜኑ ጦርነት በሰላም ስምምነት ከተጠናቀቀ በኋላ መንግስት በአማራ ክልል ላይ የያዘው አቋም ከህግ | AHADU RADIO FM 94.3

የሰሜኑ ጦርነት በሰላም ስምምነት ከተጠናቀቀ በኋላ መንግስት በአማራ ክልል ላይ የያዘው አቋም ከህግ አግባብ ውጪ መሆኑን ህብር ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታወቀ፡፡

እንደ ሃገር የሰሜኑ ክፍል ጦርነት በብዙ መልኩ ዋጋን ያስከፈለ መሆኑን አስታውሰው በህወሃት እና በፌደራል መንግስቱ መካከል በፕሪቶርያ የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተገቢ እና ትክክለኛ አማራጭ ነው ያሉት የህብር ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ኢንጂነር ይላቃል ጌትነት ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ከሰላም ስምምነቱ በኋላ መንግስት በተለየ መልኩ በአማራ ክልል ላይ የያዘው አቋም ህገ ወጥ ነው ያሉት ምክትል ሊቀመንበሩ የተለያዩ ምክንያቶችን እየሰጡ የክልሉን ዜጎች ማጉላላት እና ከህግ አግባብ ውጪ በሆኑ ድርጊቶች ማንገላታት በተደጋጋሚ እየተስተዋለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይህ ከመሆኑም ባለፈ ክልሉን የጦርነት ቀጠና ለማድረግ እየተሄደበት ያለው መንገድ አግባብ ባለመሆኑ ፓርቲያቸው ህግ እንዲከበር መንግስትን ይጠይቃል ብለዋል፡፡ ለሃገር ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ እና የዜጎች መብት መከብር መንግስት መወጣት ያለበት ሚና የላቀ ቢሆንም በዛ ልክ ግን እየሰራ አይደለም ያሉት ኢንጂነር ይልቃል ፓርቲያቸው በመንግስት በኩል የሚስተዋሉ ችግሮች በአፋጣኝ እልባት እንዲያገኙ አጽንኦት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል፡፡ ህብር ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሀገራዊ ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ በትላንትናው እለት ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en