Get Mystery Box with random crypto!

በጤና ዘርፉ ሪፖርትና ውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ላይ ወሳኝ ሚና ይጫወታል የተባለው የቀጠናዊ ጤና መረጃ | AHADU RADIO FM 94.3

በጤና ዘርፉ ሪፖርትና ውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ላይ ወሳኝ ሚና ይጫወታል የተባለው የቀጠናዊ ጤና መረጃ ስርዓት ውጤታማ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በመላ ሀገሪቱ ከተዘረጋ ስድስት አመት የሆነው ይህ የመረጃ ስርዓት ከዚህ በፊት ተቋማት በየፊናቸው በተበታተነ መልኩ የሚይዙትን መረጃ ወጥነት ባለው መልኩና በየደረጃው ያሉ የዘርፉ ሰራተኞች ተደራሽ በሆነ መልኩ ተግባራዊ መሆን እንደቻለ ተገልጻል፡፡ የመረጃ ስርአቱ በሁሉም መንግስታዊ እና ብዛት ያላቸው የግል የጤና ተቋማት ተዘርግቶ ስራ ላይ ሲሆን ባለፉት ጥቂት አመታት የኮቪድ 19 ምርመራ ክትባት እና ሌሎች አገለግሎቶችን የመረጃ ክትትል አሰራር ላይ ውጤታማ እንደነበር የገለጹት አቶ ገመቺስ መልካሙ በጤና ሚንስቴር የዲጂታል ጤና መሪ ስራ አስፈጻሚ ናቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የቲቢ ህሙማንን እንዲሁም የቢጫ ወባ ክትባት የወሰዱና ያልወሰዱ ዜጎችን መረጃ አደራጅቶ በመያዝ በኩል ወሳኝ ሚና ተጫውቷል ነው ያሉት፡፡

በሪፖርት አደራረግ በኩል የግል ክሊኒኮች በየጊዜው እየተከፈቱ መዘጋት በግሉ ዘርፍ በኩል የመረጃ ፍሰቱ ላይ ችግር መፍጠሩን ጠቁመዋል፡፡ ከዚህ ሌላ በቂ የሆነ የኢንተርኔት አገልግሎት ግንኙነት አለመኖሩ፣ የግብዓት እጥረት፣ በመረጃ ቴክኖሎጂ እና ሌሎች ተመሳሳይ ሙያዎች ላይ የሰለጠነ የሰው ሀይል በሁሉም ተቋማት አለመኖሩ ክፍተት መፍጠሩ ተመላክቷል፡፡
አክለዉም የጤና ሚንስቴርም በየአምስት አመቱ የመረጃ ስርዓቱን የማሻሻል ስራ እንደሚሰራ አስታዉቀዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24