Get Mystery Box with random crypto!

እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ባደረሰቸዉ አየር ጥቃት በርካታ ፍልስጤማዉያን ከቤት ንብረታቸዉ መፈናቀላቸዉ | AHADU RADIO FM 94.3

እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ባደረሰቸዉ አየር ጥቃት በርካታ ፍልስጤማዉያን ከቤት ንብረታቸዉ መፈናቀላቸዉ ተገልጻል፡፡

በቅርቡ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ ባደረሰችው የአየር ጥቃት 2 ሺ 516 ፍልስጤማውያንን ቤት አልባ አድርጓቸዋል ሲሉ የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል። በጋዛ የሚገኘው የማህበራዊ ልማት ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ 180 ህጻናት መኖሪያቸውን ካጡት መካከል ይገኙበታል። ሚኒስቴሩ የአረብ፣ እስላማዊ እና አለም አቀፍ ድርጅቶች በእስራኤል በጋዛ ላይ በደረሰው ጥቃት ለተጎዱ ቤተሰቦች እርዳታ እንዲያደርጉ ተማጽኗል።

የእስራኤል ጦር ባለፈው ሳምንት በጋዛ ላይ ለአምስት ቀናት በወሰደውን የአየር ድብደባ ቢያንስ 33 ፍልስጤማውያን ሲገደሉ በደርዘን የሚቆጠሩ ቆስለዋል ሲል የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታዉቋል። የፍልስጤም ቡድኖች ወደ እስራኤል ሮኬት በመተኮስ አጸፋውን ወስደው ቢያንስ ሁለት እስራኤላውያንን ገድለዋል ነዉ የተባለዉ። በግብፅ አደራዳሪነት የተኩስ አቁም ስምምነት ከሁለቱም ወገን ከቀናት በፊት ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ በሃማስ የሚመራ የመንግስት ሚዲያ ጽህፈት ቤት እስራኤል በጋዛ ላይ በፈጸመችዉ ጥቃት 2 ሺ 41 መኖሪያ ቤቶች መዉደማቸዉን አስታዉቋል። ዘገባዉ የአናዶሉ ነዉ፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24