Get Mystery Box with random crypto!

የኢራን እና የፓኪስታን መሪዎች የሁለቱን ሀገራት የድንበር ገበያ መርቀዉ መክፈታቸዉ ተገልጿል፡፡ | AHADU RADIO FM 94.3

የኢራን እና የፓኪስታን መሪዎች የሁለቱን ሀገራት የድንበር ገበያ መርቀዉ መክፈታቸዉ ተገልጿል፡፡

የኢራኑ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ እና የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሻባዝ ሻሪፍ በፓኪስታን ደቡብ ምዕራብ ባሎቺስታን ግዛት የድንበር ገበያን ከፍተዋል ነዉ የተባለዉ። የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ የትላንቱ ምርቃት "ፓኪስታን እና ኢራን የነዋሪዎችን ደህንነት ከፍ ለማድረግ ያላቸውን ጠንካራ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነዉ ብሏል፡፡ የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር በሀገራቸዉ የቴሌቪዥን ጣቢያ በተላለፈው ንግግራቸዉ ሀገራቸው የኢራን ድንበር ደህንነትን ለማሻሻል የተቻላትን ሁሉ እንደምታደርግ ለራይሲ አረጋግጠዋል፡፡ አክለውም ሁለቱም ወገኖች የንግድ እና የኢኮኖሚ ግንኙነታቸውን ለማሳደግ መስማማታቸዉን አስታዉቀዋል፡፡

በኢራን እና በፓኪስታን መካከል ያለው ግንኙነት ከዚህ ቀደም አወዛጋቢ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን እልባት እያገኘ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ ዘገባዉ፡- የኢራን ዋየር ነዉ፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24