Get Mystery Box with random crypto!

በሰሜን ሸዋ ዞን ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ሁለት ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሂደት እንዳ | AHADU RADIO FM 94.3

በሰሜን ሸዋ ዞን ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ሁለት ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሂደት እንዳቋረጡ ተነገረ፡፡

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት በዞኑ በሚገኙ ሁለት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ይሰጥ የነበረው የትምህርት አገልግሎት መቆሙን የገለጹት የሰሜን ሸዋ ዞን ትምህርት መምሪያ ምክትል ሃላፊ አቶ ታደሰ ሸዋፈራው ናቸው፡፡
ትምህርት ቤቶቹ ል አንዱ በኤፍራታና ግድም ወረዳ ጀውሃ ከተማ ላይ የሚገኝ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ በሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር የሚገኝ መሆኑን ጠቅሰው ትምህርት ቤቶቹ ላይ ግን የደረሰ ምንም አይነት ጉዳት የለም ብለዋል፡፡ ተማሪዎች በሌሎች አካባቢዎች ትምህርት እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑንም አንስተዋል፡

በአዋሳኝ አካባቢዎች በተደጋጋሚ የሚያጋጥመው የሰላም መደፍረስ ለትምህርት መቋረጡ ምክንያት መሆኑንም ገልጸው ሰላም የማምጣት ሂደቱ አስተማማኝ ሁኔታ ላይ እስኪ ደርስ መምህራንና ተማሪዎች ስጋት ውስጥ በመሆናቸው ምክንያት የተፈጠረ ነው ብለዋል፡፡በሌሎች አካባቢዎች ግን በአንጻራዊነት ሰላም በመኖሩ መደበኛ የትምህርት አሰጣጥ ሂደቱ መቀጠሉን አንስተው በዞኑ የሚገኙ 51 ትምህርት ቤቶች የዘንድሮውን የ12ተኛ ክፍል አጠቃላይ ፈተና ለመስጠት እየተዘጋጁ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24