Get Mystery Box with random crypto!

በፖለቲካ የሃሳብ ትግል ላይ የሚፈጠሩ ልዩነቶችን ወደ ተሻለ ሃሳብ ማምጣት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ፡ | AHADU RADIO FM 94.3

በፖለቲካ የሃሳብ ትግል ላይ የሚፈጠሩ ልዩነቶችን ወደ ተሻለ ሃሳብ ማምጣት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ፡፡
በቅርቡ ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ ፓርቲ አመራር የነበሩና አባላት ከፓርቲዉ ለቀዉ መዉጣታቸዉ የሚታወቅ ነዉ፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ ከፓርቲዉ መልቀቅ ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያት ምንድን ነዉ፤ ለምንስ ችግሩን ዉስጥ ሆኖ መፍታት አልተቻለም የሚለዉ ጥያቄ ከአሃዱ መድረክ የተነሳላቸዉ የቀድሞ የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሸዋስ አሰፋ በጉዳዩ ላይ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ፓርቲዉ የተነሳበትን አላማ ወደ ጎን በማድረግ የፓርቲዉ ሃሳብ ያልሆኑ ጉዳዮች ላይ ተጠምዷል ይሄ ደግሞ የሆነዉ አሁን አይደለም ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ›
አክለዉም የሚስተካከልበትን እና ወደ ቀደመዉ አቋሙ የሚመለስበትን ስራ ለመስራት ብዙ ትግል ብናደርግም ባለመሳካቱ ምክንያት ልንለቅ ተገደናል ይህ ማለትም ፓርቲዉ ሙሉ ለሙሉ በሌሎች ፓርቲዎች ሀሳብ ተዉጧል ማለት ነዉ ሲሉ ሃሳባቸዉን ገልፀዋል፡፡
በሌላ በኩል ፓርቲዉ የህዝብ እንጂ ህዝብ የፓርቲ ሊሆን ስለማይገባዉ እየተካሄደ ያለዉ ተግባር ይህን ያገናዘበ ስላልሆነ ከፓርቲዉ ለመልቀቅ ተገደናል ነዉ ያሉት፡፡ ህዝብ የሚታገልለት ፓርቲ ያስፈልገዋል ያሉት አቶ የሺዋስ አሁን ላይ ግን ከፓርቲዉ የለቀቅነዉ አባላት ቀጣይ መዳረሻችን ምን እንደሆነ ወደ ፊት የምናሳዉቅ ይሆናል ሲሉም ገልጸዋል፡፡
አክለዉም በፓርቲዉ ዉስጥ የሚታዩ ችግሮችን በመቅረፍ እና ፓርቲዉ እንደ ፓርቲ አቋሙን ይዞ መራመድ ሲኖርበት፤ አላማዉን ወደ ጎን በመተዉ በሰዉ ሀሳብ ተዉጧል ይህ ደግሞ ተስፋ አድርጎ የነበረዉን ህዝብ ያሳዘነ ነዉ ለምን ከተባለ የገዥዉ ፓርቲ እና የኢዜማ አቋም ፍፁም የማይጣጣም በመሆኑ ነዉ ሲሉ አቶ የሺዋስ አጽኖት ሰጥተዉ ተናግረዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24