Get Mystery Box with random crypto!

የስደት እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት ከተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ጋር በት | AHADU RADIO FM 94.3

የስደት እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት ከተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ጋር በትብብር ለመስራት ስምምነት ማድረጋቸዉን አስታውቀዋል፡፡
ስምምነቱን ያደረጉት ከስደት እና ስደት ተመላሾች አገልግሎትና የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን በሱማሌ ክልል የቀብሪበያህ ወረዳ ላይ በጋራ ለመስራት እንደሆነ አገልግሎቱ ለአሃዱ በላከዉ መግለጫ አስታዉቋል፡፡
በሶማሌ ክልል በቀብሪበያህ ወረዳ የሀገር ውስጥ እና ከውጪ የሚገቡ ስደተኞችን አንድ ላይ በማካተት እና የአካባቢ ውህደትን የበለጠ ለመፍጠር ያለ ስምምነት መሆኑ ተገልጻል፡፡
ከ16 ሺ በላይ ስደተኞች ላለፉት 30 ዓመታት በቀብሪበያህ ወረዳ ሲኖሩ ነበር የተባለ ሲሆን በቀብሪበያህ ወረዳ እና አካባቢው የሚገኙትን የስደተኛ መጠለያዎች ወደ ወረዳዉ በማምጣት የቤት ፣ የውሀ ፣ የኤሌትሪክ ሃይል ፣ የአስተዳደር እና ሌሎች የመሰረተ ልማቶችን በአንድ እንዲያገኙ ለማድረግ ያስችላል ተብሏል፡፡
የስደት እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋሁን ጎበዜ ከተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ጋር በጋራ ለመስራት ከስምምነት መደረሱ በአካባቢው ለሚኖሩ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጪ ስደተኞች በራስ መተማመን እና ሁለንተናዊ አገልግሎትን ለማጠናከር የሚጠቅም ነዉ ብለዋል፡፡
አክለዉም ኢትዮጵያ በአዉሮፓዉያኑ 2019 በተካሄደው ዓለም አቀፉ የስደተኞች ፎረም ወቅት የገባቻቸዉን ቃለ መሃላዎች ተግባራዊ ለማድረግ አስተዋፅኦ እንዳለዉ ጠቁመዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24