Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረዉ እርዳታ ሊቀጥል መሆኑ ተገለፀ፡፡ ወደ ትግራይ ክልል የሚገባዉ እር | AHADU RADIO FM 94.3

በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረዉ እርዳታ ሊቀጥል መሆኑ ተገለፀ፡፡
ወደ ትግራይ ክልል የሚገባዉ እርዳታ በተለያዩ ህገ ወጥ ምክንያቶች ተቋርጦ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን በዚህም ቁጥራቸዉ ቀላል የማይባል ዜጎች ለከፋ የምግብ እጦት ተዳርገዉ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡
የአለም የምግብ ፕሮግራም እንዲሁም የአሜሪካዉ ተራድኦ ድርጅት ዩ ኤስ አይ ዲ እየተላኩ ያሉት የእርዳታ ቁሳቁሶች በአግባቡ እየደረሱ ባለመሆኑ ምክንያት ድርጊቶቹ እስኪጣሩ ድረስ እርዳታ ማቋረጡን አሳዉቆ ነበር ፡፡
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የፌደራል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለአሐዱ በሰጠዉ መረጃ መሰረት የእርዳታ ስራዉ መልሶ ሊቀጥል መሆኑን አመላክቷል፡፡
በዚህም በሚቀጥሉት 72 ሰአታት ዉስጥ እረዳታዎችን የመዉሰድ ስራዉ ሊጀመር እንደሚችል የተናገሩት የፌደራል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዉ አቶ አታለል አቡሃይ ናቸዉ፡፡
ተፈጥሮ የነበረዉን ችግር ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር በመሆን ክትትል እናደርጋለን ነገር ግን እርዳታዉ መቀጠል አለበት በሚል በተደረገዉ ዉይይት መሰረት እንዲቀጥል መደረጉንም አንስተዋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከሰሞኑ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የአሜሪካዉ ተወካይ ማይክ ሀመር በቀጠናዉ ባሉ ችግሮች ላይ እና በፕሪቶሪያ ስለተደረገዉ የሰላም ስምምነት አተገባበር ዉይይታ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ይታወቃል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24