Get Mystery Box with random crypto!

የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በብሩንዲ ያደረጉት ጉብኝት ተልዕኮውን እንዳላሳካ ተነገረ ብሩንዲ የ | AHADU RADIO FM 94.3

የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በብሩንዲ ያደረጉት ጉብኝት ተልዕኮውን እንዳላሳካ ተነገረ
ብሩንዲ የሞስኮውን ከፍተኛ ዲፕሎማት ሰርጌ ላቭሮቭን ተቀብላ ያስተናገደች ቢሆንም የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ በዩክሬን ላይ አቋም እንድትይዝ ያደረጉት ሙከራ አለመሳካቱ ነው የተነገረው፡፡
ብሩንዲም በዩክሬንና ሩሲያ ጉዳይ ላይ ገለልተኛ አቋም እንዳላት አሳውቃለች ነው የተባለው፡፡
የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አልበርት ሺንጊሮ ከሩሲያው አቻቸው ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር በዋና ከተማዋ ቡጁምቡራ ተገናኝተው ዝግ ስብሰባ ማድረጋቸው ታዉቋል፡፡
አንበርት ከስብሰባው በኋላ በሰጡት መግለጫም ብሩንዲ በመፍተሄው እንጂ በችግሩ ላይ አቋም መያዝ አትፈልግም፡፡ ብሩንዲ እንደማንኛውም ሀገር ሉአላዊት ሀገር ስትሆን አጋሮቻችንን የምንመርጠው በህዝባችን ፍላጎት ላይ ተመስርተን ነው
ብለዋል፡፡
አያይዘውም የቡርንዲ መንግስት በግጭት ላይ የሚገኙ ወገኖች በተቻለ ፍጥነት ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት እንዲመጡ እንደሚመክርና ይህም ሀገሪቱ የምትከተለው የውጭ ጉዳይ መርህ መሆኑን አስታውቀዋል ተብሏል፡፡
ዘገባው፡-የዘ ኢስት አፍሪካ ነው፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24