Get Mystery Box with random crypto!

የክልል የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሀሰተኛ የትምህርትና ሲኦሲ ማስረጃዎች መበራከታቸው ተገለጸ፡ | AHADU RADIO FM 94.3

የክልል የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሀሰተኛ የትምህርትና ሲኦሲ ማስረጃዎች መበራከታቸው ተገለጸ፡፡
በሀገሪቱ ከክልል የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚመጡ የድፕሎማ የትምህርት እና ሲኦሲ ማስረጃዎች ሀሰተኝነት አብዛኛዉን ቁጥር መያዙን የተናገሩት በኢፌድሪ ትምህርት እና ስልጠና ባለ ስልጣን የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ እና አቻ ግመታ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ሀብታሙ ገብረ መድህን ናቸው፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ሲሰራ እንደቆየና ጉድለቶች እየታዩ በተለይም ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችን በተመለከተ የተለያዩ እርምጃዎች ሲዎሰድ እንደቆየ ጠቁመዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማስረጃዎችም ሊፈተሹ የሚገባቸዉ በመሆኑ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ወደ ተግባር ለመግባት ዝግጅቶችን እንዳጠናቀቀ ነው የተናገሩት፡፡
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የተማሪዎቻቸዉን መረጃ አሟልተዉ እንዲልኩ የተጠየቁ የግል ከፍተኛ ትምህርተ ተቋማት አብዛኞቹ አጠናቀዉ ማስገባታቸዉን እና ቀሪዎቹም በቅርብ ጊዜ ውስጥ አጠናቀዉ እንደሚያስገቡ ይጠበቃል ሲሉ ለአሀዱ ገልጸዋል፡፡
የግልም ሆኑ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርተ ተቋማት ተማሪዎች በዘንደሮዉ አመት የሚሰጠዉን የመዉጫ ፈተና በአግባቡ እንዲዎስዱና ከሀሰተኛ መረጃ እራሳቸዉን እንዲጠብቁም መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24