Get Mystery Box with random crypto!

በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የደረሰዉ የማሀበራዊ እና ስነ-ልቦናዊ ቀውስ ትኩረት ሊሰጠዉ እንደሚገባ ተ | AHADU RADIO FM 94.3

በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የደረሰዉ የማሀበራዊ እና ስነ-ልቦናዊ ቀውስ ትኩረት ሊሰጠዉ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ከደረሰዉ ህልፈተ ህይዎት እና የንብረት ዉድመት ባሻገር የስነ ልቦና ቀውስ እና የማሀበራዊ እሴቶች መፈራረስ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸውን የስነ ልቦና ባለሙያዎች አሳስበዋል፡፡ ጉዳዩ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን የሚጠይቅ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
የነፃነት እና አና እኩልነት ፓርቲ ባዘጋጀዉ የድህረ ጦርነት ማገገሚያ መርሃ ግብር ላይ በጦረነቱ የደረሰዉን ዉድመት አስመልክቶ የስነ ልቦና ባለሙያዋ እጩ ዶክተር ሰብለ ሃይሉ ጥናታዊ ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡ የደረሰዉን የገንዘብ ዉድመት እና ህልፈተ ህይዎት በቁጥር ስናስቀምጥ በስነ ልቦና የተጎዱትን እና የፈረሱ ማህበራዊ መስተጋብሮችን በምንም ልንለካቸዉ አንችልም ነገር ግን የጉዳቱ ጥልቀት እና ስፋት ከፍተኛ ትኩረት ይሻል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ኢትዮጵያ ባላት የጦርነት ታሪክ ዉስጥ ሰለባ የሆኑ እና ጉዳት የደረሰባቸዉ የማህበረሰብ ክፍሎች ትኩርት ሲሰጣቸዉ አይታይም ይህም ሀገሪቷ በተደጋጋሚ ለምትገባበት የጦርነት አዙሪት አንዱ ምክንያት ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24