Get Mystery Box with random crypto!

ጋና የእንግሊዝ ሙዚየም የተሰረቁ ወርቆቼን መመለስ አለበት አለች፡፡ በጋና ዋና ከሚባሉ ጎሳዎች አ | AHADU RADIO FM 94.3

ጋና የእንግሊዝ ሙዚየም የተሰረቁ ወርቆቼን መመለስ አለበት አለች፡፡

በጋና ዋና ከሚባሉ ጎሳዎች አንዱ የሆነው የሆነው የአሻንቴ ጎሳ መሪ የእንግሊዝ ሙዚየም የተሰረቁ ወርቆችን እንዲመልስ መጠየቃቸው ተዘግቧል፡፡
ቅርሶቹ በሚመለሱበት ሁኔታም የጎሳው መሪ ከሙዚየሙ ዳይሬክተር ጋር መነጋገራቸው ተነግሯል፡፡
እንዲመለሱ የተጠየቁት በፈረንጆቹ 1874 ከእንግሊዞች ጋር በነበረ ጦርነት ከአሻንቴ ቤተ መንግስት የተወሰዱ ቅርሶችንም ያጠቃልላል ነው የተባለው፡፡

በእንግሊዝ ወታደሮች የተወሰዱ ሁለት መቶ ያህል የወርቅ ቁሶች በሙዚየሙ ውስጥ እንደሚገኙ ተዘግቧል፡፡ የሙዚየሙ ቃል አቀባይ የሶሰተኛው አንግሎ አሻንቴ ጦርነት መጠናቀቅ አስመልክቶ የመቶ ሀምሳኛ እዩቤልዩ ሲከበር ከቅርሶቹ ስብስብ የተወሰኑትን በውሰት የሚሰጡበት ሁኔታዎች እየተጤኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ዘገባው፡-የየዘ ቮይስ ኒውስ ነው፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24