Get Mystery Box with random crypto!

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸረ ማሰቃየት ኮሚቴ ያወጣው ሪፖርት አዲስ አይደሉም ሲል የኢትዮጵያ | AHADU RADIO FM 94.3

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸረ ማሰቃየት ኮሚቴ ያወጣው ሪፖርት አዲስ አይደሉም ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ በአለም ዓቀፍ ደረጃ ካጸደቀቻቸው የሰብአዊ መብት ስምምነቶች መካከል አንዱ የሆነው እና በ1994 አጽድቃ አባል የሆነችበት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸረ ማሰቃየት ኮሚቴ በኢትዮጵያ ያለውን የታራሚዎች አያያዝ እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ ባሳለፍነው አርብ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ አሐዱ መግለጫው ዙሪያ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ኮሚሽነር ዶክተር አብዲ ጅብሪልን አነጋግሯል፡፡

ኮሚቴው አሳስቦኛል ያለው በኢትዮጵያ ግጭት ባለባቸው የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እና በማረሚያ ቤት ያለው ኢ-ሰብአዊ አያያዝ እነ እሱም ከዚህ በፊት በተለያየ ጊዜ ባወጧቸው ሪፖርቶች የተገለጹ ሲሆን፡፡ ለዚህም መንግስት አስፈላጊውን እርምጃ እወስዳለሁ ብሎ ወደ ስራ መግባቱን እና ተጠያቂዎችን ለፍርድ ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን አንስተው የኮሚቴው ሪፖርት አጽንኦት ለመስጠት እንጂ አዲስ ጉዳይ አይደለም ብለዋል፡፡
ኮሚቴው በስምምነቱ አባል የሆኑ ሃገራትን በሰብአዊ መብት አያያዝ ያስመዘገቡትን በጎ ውጤት እና ያጋጠሙ ችግሮችን የሚገልጽ እንጂ በፍርድ ቤት ደረጃ አከራክሮ አንዱን ጥፋተኛ ሌላውን ተጠቂ የሚያደርግ አይደለም ሲሉም ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24