Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ክልል በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1 ሺ 2 መቶ 31 ያልመከኑ ፈንጂዎች መገኘታቸው ተ | AHADU RADIO FM 94.3

በትግራይ ክልል በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1 ሺ 2 መቶ 31 ያልመከኑ ፈንጂዎች መገኘታቸው ተገለጸ፡፡
በሀገሪቱ በሰሜኑ ክፍል በነበረው ጦርነት ጉዳት ከደረሰባቸው ተቋማት አንዱ ትምህርት ቤቶች በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳሉ፡፡
ከሰላም ስምምነቱ በኃላ 1 ሺ 2 መቶ 18 ትምህርት ቤቶች የተከፈቱ ሲሆን 7 መቶ 22ቱ የሚሆኑት በደረሰባቸው ከባድ ጉዳት አገልግሎት አለመጀመራቸውን ለአሐዱ የተናገሩት የህጻናት አደን ድርጅት በኢትዮጵያ /ሴቭ ዘ ችልድረን/ የትግራይ ክልል አስተተባባሪ አቶ አታክልቲ ገብረ ዩሀንስ ናቸው፡፡
ተማሪዎች 3 ዓመት የትምህርት ገበታቸው ላይ አለመገኘታቸውን ያነሱት አስተባባሪው አሁን ላይ ለ39 ሺ መምህራን የ3 ወር ደሞዝ መከፈሉን ተናግረዋል፡፡
ትምህርት ቤቶችን ከስጋት ነጻ ለማድረግ እና የተማሪዎቹ ደህንነት እንዲጠበቅ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸውን እና ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ጋር በተሰራው ስራ በ1ሺ 544 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1 ሺ 2 መቶ 31 ያልመከኑ ፈንጂዎች መገኘታቸውን አንስተዋል፡፡
ድርጅቱ የተሸከርካሪ እና ሌሎች ድጋፎችን በማድረግ በጋራ በተሰራው ስራ ትምህርት ቤቶችን ከስጋት ነጻ ማድረግ እንደተቻለም ተናግረዋል፡፡ለ40ሺ ተማሪዎች በ59 ትምህርት ቤቶች ላይ የህጻናት አደን ድርጅት በኢትዮጵያ/ የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጉን አመላክተዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24