Get Mystery Box with random crypto!

የማኀበራዊ ጥበቃ አገልግሎቶችን የሚፈልጉ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ ቢሆንም አፈጻጸሙ ግን አነስተኛ መሆኑ | AHADU RADIO FM 94.3

የማኀበራዊ ጥበቃ አገልግሎቶችን የሚፈልጉ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ ቢሆንም አፈጻጸሙ ግን አነስተኛ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የማህበራዊ ጥበቃ ፕሮግራሞችን በተለያዩ የመንግስት እና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት የሚተገበሩ በመሆናቸዉ አቀናጅቶ ለመምራት እና አፈፃፀሙን ለማሳደግ ብሄራዊ የማህበራዊ ጥበቃ ፖሊሲ እና የማስፈፀሚያ ስትራቴጂ ተቀርፆ በመተግበር ላይ እንደሚገኝ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር አስታዉቋል፡፡ የማኀበራዊ ጥበቃ አገልግሎቶችን የሚፈልጉ ዜጎች ቁጥር በየጊዜው በሚከሰቱ ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሠራሽ ችግሮች ምክንያት እየጨመረ ቢሆንም የፖሊሲዉ አፈጻጸም ግን አነስተኛ መሆኑን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ተናግረዋል።

ፖሊሲውን እና የማስፈጸሚያ ስትራቴጂውን በሚገባ በመተግበር እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል ጠንካራ የማኀበራዊ ጥበቃ ሥርዓት መዘርጋት እንደሚገባ ገልፀዉ ለዚህም የሚመለከታቸው አካላት ርብርብ ወሳኝ እንደኾነ ገልፀዋል። አሁን ካለው ዓለማቀፋዊ እና ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታ አኳያ የማኀበራዊ ጥበቃ አገልግሎቶችን በማሳደግ ፤ሥርዓትን የመገንባት አስፈላጊነትና ጠቀሜታውን በማሳወቅ የተለያዩ አካላትን ግንዛቤ የማሳደግ ስራ እንደሚሰራ አክለዋል

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24