Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያውያን ለውጪ አገራት የስራ ስምሪት በሚጓዙባቸው አገራት ከሚገኙ የሰራተኛ ማህበራት በኩል የ | AHADU RADIO FM 94.3

ኢትዮጵያውያን ለውጪ አገራት የስራ ስምሪት በሚጓዙባቸው አገራት ከሚገኙ የሰራተኛ ማህበራት በኩል የህግ ከለላ እንዲያገኙ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ለውጪ አገር የስራ ስምሪት በዋናነት የአረብ አገራትን ተመራጭ እንደሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በእነዚህ አገራት በስራ ላይ ለሚደርስባቸው በደሎች እና መሰል ጉዳዮች የህግ ከለላ እንዲያገኙ የሚያስችሉ ስምምነቶች መደረጋቸውን የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ አስታውቀዋል፡፡ ብዙ ኢትዮጵያውያን ከሚገኙባቸው የአረብ ሀገራት መካከል ሊባኖስ እና ኩዌይት ተጠቃሽ ሲሆኑ በእነዚህ አገራት የሚገኙ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽኖች ለኢትዮጵያውያን ሰራተኞችም የህግ ከለላ እንዲሰጡ የሚያስችሉ ስምምነቶችን በመፈራረም በጋራ እየሰሩ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም ሌላኛዎቹ የኢትዮጵያውያን መዳረሻ ከሆኑት ኳታር ፣ ባህሬን እና ኦማን የሰራተኛ ማህበራት ጋር በመነጋገር ላይ የሚገኙ ሲሆን በቅርብ ጊዜ ውስጥ ስምምነት እንደሚፈራረሙ እና የዜጎችን ደህንነት የማስጠበቅ ስራን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም በሳውዲ አረቢያም መሰል ስምምነቶችን ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት የተደረገ ቢሆንም በአገሪቱ ምንም አይነት የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ባለመኖሩ ምክንያት እስካሁን ውጤታማ ሊሆን እንዳልቻለ አመላክተዋል::

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24