Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ክልል የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም እና አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ እንደሆነ | AHADU RADIO FM 94.3

በትግራይ ክልል የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም እና አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

የፕሪቶርያውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በትግራይ ክልል በጦርነቱ ምክንያት የወደሙ ተቋማትን መልሶ የመገንባት ስራዎች በመንግስትም ሆነ በተራድኦ ተቋማት በኩል እየተሰሩ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ከደረሰባቸው አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መካከል የጤናው ዘርፍ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባም እሙን ነው፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ መስኮች ከተሰማሩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው የህጻናት አድን ድርጅት በትግራይ ክልል በጦርነቱ ምክንያት የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ በኢትዮጵያ የህጻናት አድን ድርጅት የትግራይ ክልል አስተባባሪ አቶ አታክልቲ ገብረ ዮሃንስ ለአሃዱ ተናግረዋል፡፡

በጦርነቱ ምክንያት ድርጅቱ የሚሰራባቸው የጤና ተቋማት ወድመው እንደነበር ያስታወሱት አስተባባሪው ከሰላም ስምምነቱ በኋላ እነዚህን የጤና ተቋማት መልሶ ለማቋቋም በካታ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል፡፡ የጤናው ዘርፍ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ በመሆኑ የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም ጥረት መደረጉ ተገቢ መሆኑን ያነሱት አስተባባሪው፤ ከጤናው ዘርፍ በተጨማሪ በሌሎች ድርጅቱ በሚሰራባቸው ማህበራዊ ጉዳዮች ላይም ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24