Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ጥሩ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲፈጠር የሁለቱ ሀገራት ድንበር በሆነ | AHADU RADIO FM 94.3

በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ጥሩ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲፈጠር የሁለቱ ሀገራት ድንበር በሆነችው በትግራይ ክልል ላይ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን ሁለቱም ሀገራት መስራት እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡

የኤርትራ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ከኢትዮጵያ ጋር ያለንን ግንኙነት ለማሻከር የሚጥሩ ሃይሎች አሉ ሲሉ በቅርቡ በትዊተር ገፃቸው ላይ መፃፋቸውን ተከትሎ አሐዱም እነዚህ ጣልቃ የሚገቡ ሀገራት እነማን ሊሆኑ ይችላሉ ሁለቱ ሀገራትስ ምን ማድረግ አለባቸው ሲል የፖለቲካ እና ዓለማቀፍ ግንኙነት ምሁራንን አነጋግሯል፡፡
የፖለቲካ እና ዓለማቀፍ ግንኙነት መምህሩ አቶ ግደይ ደገፉ እንደሚሉት አሁንም ኤርትራ በትግራይ ክልል በኩል በኢትዮጵያ ላይ በተደጋጋሚ ድንበር አልፋ በምታደርገው እና በምታሳየው አቋም ምክንያት የውጪ ሀገራት ጣልቃ መግብታቸው ጥሩ ነው ፣ እነዚህ ጣልቃ የሚገቡት ሀገራትም ምናልባትም አሜሪካ እና አውሮፓውያኑ ናቸው፡፡
በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ጥሩ ግንኙነት እንዲፈጠር በትግራይ ክልል ሰላም እና መረጋጋት እንዲፈጠር ሁለቱ ሀገራት መስራት አለባቸው ብለዋል፡፡

ሌላኛው የፖለቲካ እና ዓለማቀፍ ግንኙነት መምህር ዶክተር ደጉ አስረስ በበኩላቸው በቅርቡ የኢትዮጵያ መንግስትም አንዳንድ የውጪ አካላት ጣልቃ እየገቡብኝ ነው በሚል መግለፁ ታወሳል፣ በተመሳሳይ የኤርትራ መንግስትም ይሄንን ሲናገር ለሁለቱም ህዝቦች በግልጽ እነማን እንደሆኑ መገለጽ ነበረበት ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ያለው አለመረጋጋት ለሀገሪቱም ሆነ ለቀጠናው የሚፈጥረው ስጋት ስላለው በተለይ ምራባውያኑ ጉዳዩን ለማስተካከል ጣልቃ ሊገቡ ይችላሉ ብለዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP