Get Mystery Box with random crypto!

AHADU RADIO FM 94.3

የቴሌግራም ቻናል አርማ ahaduradio — AHADU RADIO FM 94.3 A
የቴሌግራም ቻናል አርማ ahaduradio — AHADU RADIO FM 94.3
የሰርጥ አድራሻ: @ahaduradio
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.23K
የሰርጥ መግለጫ

አሐዱ ራድዮ 94.3
Your source for top local and international news and analysis.
"Voice of Ethiopian"
የአሐዱ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ወቅታዊና እውነተኛ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-03-10 13:36:15
ድርቅ በተከሰተባቸው የሀገራችን አካባቢዎች የሚገኙ ብሄራዊ ፓርኮች ውስጥ ያሉ የዱር እንስሳት ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደሚገኙ ተገለፀ፡፡

በሀገራችን የተወሰኑ አካባቢዎች ላይ የተከሰተው ድርቅ በአካባቢው ከሚኖረው የማህበረሰብ ክፍል በተጨማሪም በእነዚሁ አካባቢዎች አቅራቢያ የሚገኙት ሁለት ብሄራዊ ፓርኮች ከፍተኛ አደጋ ላይ እንዲወድቁ ማድረጉን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የኮምዩኒኬሽን ባለሙያ አቶ ናቃቸው ብርሌ አስታውቀዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በዋናነት ከፍተኛ ስጋት ያለበት የቦረና ብሄራዊ ፓርክ ሲሆን ሌላኛው በድርቁ ምክንያት ስጋት ላይ የሚገኘው ደግሞ በራህሌ ብሄራዊ ፓርክ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ እንደ የሜዳ አህያ ፣ ከርከሮ እና ሌሎችም በቦረና ብሄራዊ ፓርክ ውስጥ የሚገኙ የዱር እንሰሳት በድርቁ ምክንያት አደጋ የተደቀነባቸው እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ ድርቅ ለደረሰባቸው አካባቢዎች የተሰጠው ትኩረት እና ድጋፍ የሚበረታታ ቢሆንም ለፓርኮች እና ለዱር እንስሳቱ የተሰጠው ትኩረት ግን ዝቅተኛ እንደሆነ ገልጸው አሁን ላይ ከክልሉ ደን እና የዱር እንስሳት ድርጅት እንዲሁም የዱር እንስሳት ላይ ትኩረታቸውን አድርገው ከሚሰሩ አለማቀፍ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ውሃ እና መኖ እንዲቀርብላቸው እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡
አክለውም በእነዚህ አካባቢዎች ያሉ የዱር እንስሳትን ለመታደግ በቅድሚያ ማህበረሰቡን መታደግ ዋነኛዉ እንደመሆኑ መጠን ከሚመለከታቸዉ ተቋማት ጋር በመተባበር ለማህበረሰቡ የተለያዩ የምግብ እና አስቸኳይ እርዳታዎች ድጋፍ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
1.5K views10:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 13:30:48
እንስሳት ከአንድ አካባቢ ወደ ሌላ አካባቢ ሲንቀሳቀሱ የሚጠቀሙባቸው የምገባ ማእከላት መዘጋጀታቸው ተገለጸ፡፡

ይህንን ያሉት በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪው ዶክተር የሃንስ ግርማ ሲሆኑ ድርቁ በከፋባቸው አካባቢዎች ያሉ አርብቶ አደሮች ቀያቸዉን ለቀው ለእንስሳቱ የሚሆን የግጦሽ ሳር ወደ አለባቸው ቦታዎች እንደሚሄዱ ተናግረዋል፡፡

በአንዳንድ አካባቢዎች ያሉ አርብቶ አደሮች እንደ ኬንያና ሱዳን ያሉ አጎራባች ሃገራትን ተሻግረው ቢሄዱም እነሱም በድርቅ የተጠቁ በመሆናቸው የተሻለ ነው ያልነዉን የእንስሳት ምገባ ማእከልን ተደራሽ የማድረግ አማራጭ ወስደናል ነው ያሉት፡፡
በአብዛኛው ከተለያዩ አካባቢዎች እንስሳቶቻቸውን ይዘው የሚንቀሳቀሱ አርብቶ አደሮች ወደ ኦሮምያና ደቡብ ክልል የግጦሽ ሳር በብዛት የሚገኝባቸው ቦታዎች ይዘው እንደሚሄዱ የገለጹት አማካሪው በእነዚሁ አካባቢዎች ማእከላቱ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ከክልልና ዞን ቢሮዎች ጋር መወያታቸውን ተናግረዋል ፡፡

አንዳንድ የኢትዮጵያ፣ የሶማሊያ እና የኬንያ አካባቢዎች ለአምስት ተከታታይ ወቅቶች ዝናብ አለማግኘታቸውን ተከትሎ ሚሊዮኖችን ለምግብ እጥረት እንደሚያጋልጥ ዓለም አቀፍ ተቋማት ሲያሳስቡ ቆይተዋል።
የተለያዩ የአገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በአሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ ሲገልጹ የዓለም ጤና ድርጅትም አሃዙን 24 ሚሊዮን ስለመድረሱ መግለጹ አይዘነጋም።

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
1.6K viewsedited  10:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 12:16:06
ቡርኪራፋሶ በጂሃድ ሀይሎች ላይ የተጀመረውን ጥቃት ለማጠናከር ስዓት እላፊ ገደብ መጣሏ ተነግሯል፡፡

ቡርኪናፋሶ በስተ ሰሜንና በማእከላዊ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል የጀመረችውን የጂሃዲስቶች ጥቃት አጠናክራ ለመቀጠል በሚል የስዓት እላፊ ገደብ መጣሏን አስታውቃለች፡፡

በሳህል ቀጣና ያለችዋን በድህነት የምትጠቀሰዋ ሀገር ቡርኪናፋሶ ለረዥም ጊዜ በተካሄደባት የጂሃድ ሀይሎችና የአሸባሪዎች ጥቃት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ንጹሃንን የፖሊስና የጦር ሀይል አባላት ህይወታቸውን እንዳጡ ሲገለፅ ከሁለት ሚሊየን በላይ ሰዎች ከቤት ንብረታቸውና ከቀያቸው መፈናቀላቸው ይታወቃል፡፡

ከትናንት ምሽት ጀምሮ በቡርኪናፋሶ የተጣለው የስዓት እላፊ ገደብ የሰዎችን እንቅስቃሴ እንዲሁም የሁለት እግርና የአራት እግር ተሸከርካሪዎችም እንዳይንቀሳቀሱ የሚከለክል ነው፡፡

በቡርኪናፋሶ ከማሊ አዋሳኝ በምትገኘዋ ኮል ፔሎጎ ግዛት የተጣለው የስዓት እላፊ ገደብ የተያዘው የመጋቢት ወር እስኪጠናቀቅ ድረስ እንደሚቆይ የዘገበው ኔሽን ነው፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahadutelevision
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦ https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
2.8K viewsedited  09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 12:05:34
በዓለም ላይ የሚገኙት የውሃ አካላት መበከል ያሳሰባቸው በርካታ ሀገራት አንድ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ተገልጿል፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና መቀመጫ ኒውዮርክ ውስጥ የተፈረመውንና የውቅያኖስ ውሃ ጤንነትን ለመጠበቅ በተደረሰው የስምምነትና የመግባቢያ ሰነድ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩት ከ190 በላይ ሀገራት መሆናቸው ነው የተሰማው፡፡

እነዚያ ከአንድ መቶ ዘጠና በላይ ሀገራት የተፈራረሙት ይኸው ሰነድ ደግሞ በዓለም ታሪክ ትልቁ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስምምነት መሆኑ ተነግሮለታል፡፡ የዚሁ ስምምነት ዋና አካል ሰላሳ በመቶውን የዓለም የውቅያኖስ ውሃ ጥበቃና እንክብካቤ የማድረግና እስከ አውሮፓውያኑ 2030 ድረስ ወደ ነበረበት ይዘቱ እንዲመለስ ከተለያዩ ሰው ሰራሽ ብክለቶች የሚጠበቅ እንደሆነም ተገልጻል፡፡

ዘገባው፡-የአግዚዮስ ነው፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahadutelevision
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦ https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
2.6K viewsedited  09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 12:00:45
በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ያለፍርድ የታሰሩ ሰዎች እንግልትና ድብደባ እየደረሰባቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ አስታዉቋል፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው የሰላምና ፀጥታ ችግር ምክንያት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደር የፈረሰ መሆኑን እና ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ እንደ አዲስ የዞን አስተዳደር ቢቋቋምም በአካባቢው የፍርድ ቤትና አቃቢ ሕግ ቢሮዎች ተቋቁመው ሥራ ባለመጀመራቸው የአካባቢው ሰዎች ያለአግባብ እስር እየተፈጸመባቸው መሆኑን ኢሰመጉ አስታውቋል፡፡
መንግሥት በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በፍርድ ቤትና ዓቃቤ ሕግ ዕጦት ምክንያት እየተጣሰ ያለውን ፍትሕ የማግኘት መብትና እየደረሰ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲያስቆም ጠይቋል፡፡

ለእስር የተዳረጉ ሰዎች ያለምንም ከሳሽ በፖሊስ ጣቢያ እንግልትና ድብደባ እየደረሰባቸው ለረዥም ጊዜ ማለትም ከሁለት እስከ ዘጠኝ ወራት ታስረው እንደሚገኙ ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለማወቅ መቻሉን ገልጻል፡፡
የሰዎችን ፍትህ የማግኘት መብት ለማስጠበቅ የፍትህ ተቋማት ሥራቸውን በአግባቡ መሥራት ባለመቻላቸው ያለ ከሳሽ በፖሊስ ጣቢያ የታሰሩ ሰዎች እንግልትና ድብደባ እየደረሰባቸው መሆኑን አመላክቷል፡፡

በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የሚመለከተው የፍትሕ አካል በፍርድ ቤት የዋስትና መብታቸው እንዲጠበቅ ትዕዛዝ የተላለፈላቸዉን እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈታና ለረዥም ወራት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ታስረው የሚገኙትን ሰዎች ፍርድ ቤት በማቅረብ ፍትሕ የማግኘት መብታቸውን እንዲያስጠብቅ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ጠይቋል፡፡
2.1K viewsedited  09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 11:58:28
በትግራይ ክልል የሚገኙት ሼባ ሌዘር እና ሰማያት የእምነበረድ ፋብሪካ ሙሉ ለሙሉ እንደወደሙና ሰራተኞቹ የት እንዳሉ እንደማይታወቅ የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌድሬሽን አስታወቀ፡፡
በትግራይ ክልል ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ክልሉ የተጎዘዉ የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌድሬሽን በክልሉ ቅርንጫፍ ፅፈት ቤት እና ከ70 ሺ በላይ አባል ያለዉ ሲሆን በክልሉ ባደረገዉ ጉብኝት ሼባ ሌዘር እና ሰማያት የእምነበረድ ፋብሪካን ሙሉ ለሙሉ መዉደማቸዉን መመልከት እንደቻሉ የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌድሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሰሁን ፎሎ ለአሀዱ ተናግረዋል፡፡

አንደኛዉ ፋብሪካ 1200 ሰራተኞች ያሉት ሲሆን ሌላኛዉ ፋብሪካ ደግሞ 600 ሰራተኛ የያዘ መሆኑን ገልፀዉ ሆኖም ግን በአሁኑ ሰአት ሰራተኞች የት እንዳሉ እንደማያዉቁ የፋብሪካዎቹ አመራሮች እንደገለፁላቸዉ አስታዉቀዋል፡፡

ሁለቱ ፋብሪካዎች ሙሉ ለሙሉ በመዉደማቸዉ ምክንያት በድጋሚ ስራ ለመጀመር አደጋች መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም አልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ሙሉ ለሙሉ መዉደሙን እና ከምእራብ ትግራይ ከወልቃይት ስኳር ፋብሪካ እና ከህይወት እርሻ መካናይዜሽን ተፈናቅለዉ መቀሌ የሚገኙ ሰራተኞች መኖራቸዉን ተናግረዋል፡፡

መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ እና አዲግራት መድሀኒት ፋብሪካ በከፊል ስራ መጀመራቸዉን አቶ ካሳሁን አስታዉቀዋል፡፡
ስራ ያልጀመሩ ፋብሪካዎች ተጠግነዉ ስራ መጀመር አንዲችሉ በክልሉ መንግስት እና በፌደራል መንግስቱ በኩል ድጋፍ ሊደረግላቸዉ ይገባል ነዉ ያሉት፡፡
ስራ በጀመሩ ፋብሪካዎች ዉስጥ ለሚሰሩ ሰራተኞች የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌድሬሽን ስልጠና እንደሚሰጥ አቶ ካሳሁን አክለዉ ተናግረዋል፡፡
2.1K viewsedited  08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 11:38:04
በሃገሪቱ በርካታ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ እየተባባሰ መምጣቱን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
ካለፈው አመት አጋማሽ አንስቶ በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ በተለይም በኦሮምያ ፣ ሱማሌ ፣ አፋር ፣ ደቡብና ደቡብ ምእራብ ክልሎች ከፍተኛ ጉዳትን ያስከተለ ሲሆን በተለይም የኦሮምያና ሱማሌ ክልል አርብቶ አደር አካባቢዎች ከፍተኛው ጉዳት የተመዘገበባቸው አካባቢዎች እንደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
አሃዱም ጉዳዩ በዋነኝነት የሚመለከተው የግብርና ሚኒስቴር ድርቁን በተመለከተ መረጃን በቶሎ ለህዝብ የማይገልጽ መሆኑን ተከትሎ ምን እየሰራችሁ ትገኛላችሁ ሲል ጥያቄ አቅርቧል፡፡
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የእንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪው ዶክተር ዮሃንስ ግርማም ድርቁ ሰፋፊ የአርብቶ አደር አካባቢዎች ላይ እየከፋ መምጣቱን ተከትሎ ለአርብቶ አደሮች የእንስሳት መኖን የማቅረብ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
በተለይም ድርቁ በከፍተኛ ሁኔታ ያጠቃቸው በኦሮምያ ክልል ቦረና ዞን እንዲሁም በሶማሌ ክልል ዳዋ ዞን መኖን በከፍተኛ መጠን በማቅረብ የእንስሳቱን ብሎም የአርብቶ አደሩን ህይወት ለመታደግ ጥረት እያደረግን ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡
እስካሁን ባለው ሁኔታ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ እንስሳት በድርቁ ምክንያት መሞታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችና ሌሎች ምንጮች በተደጋጋሚ እየገለጹ ቢሆንም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ግን አሃዙን ከመግለጽ ተቆጥቧል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahadutelevision
108 views08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 11:36:45
በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ያለፍርድ የታሰሩ ሰዎች እንግልትና ድብደባ እየደረሰባቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ አስታዉቋል፡፡
በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው የሰላምና ፀጥታ ችግር ምክንያት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደር የፈረሰ መሆኑን እና ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ እንደ አዲስ የዞን አስተዳደር ቢቋቋምም በአካባቢው የፍርድ ቤትና አቃቢ ሕግ ቢሮዎች ተቋቁመው ሥራ ባለመጀመራቸው የአካባቢው ሰዎች ያለአግባብ እስር እየተፈጸመባቸው መሆኑን ኢሰመጉ አስታውቋል፡፡
መንግሥት በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በፍርድ ቤትና ዓቃቤ ሕግ ዕጦት ምክንያት እየተጣሰ ያለውን ፍትሕ የማግኘት መብትና እየደረሰ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲያስቆም ጠይቋል፡፡
ለእስር የተዳረጉ ሰዎች ያለምንም ከሳሽ በፖሊስ ጣቢያ እንግልትና ድብደባ እየደረሰባቸው ለረዥም ጊዜ ማለትም ከሁለት እስከ ዘጠኝ ወራት ታስረው እንደሚገኙ ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለማወቅ መቻሉን ገልጻል፡፡
የሰዎችን ፍትህ የማግኘት መብት ለማስጠበቅ የፍትህ ተቋማት ሥራቸውን በአግባቡ መሥራት ባለመቻላቸው ያለ ከሳሽ በፖሊስ ጣቢያ የታሰሩ ሰዎች እንግልትና ድብደባ እየደረሰባቸው መሆኑን አመላክቷል፡፡
በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የሚመለከተው የፍትሕ አካል በፍርድ ቤት የዋስትና መብታቸው እንዲጠበቅ ትዕዛዝ የተላለፈላቸዉን እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈታና ለረዥም ወራት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ታስረው የሚገኙትን ሰዎች ፍርድ ቤት በማቅረብ ፍትሕ የማግኘት መብታቸውን እንዲያስጠብቅ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ጠይቋል፡፡
163 views08:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 11:34:41
በዋግ ኽምራ ዞን በእርዳታ እጥረትና በህክምና እጦት ምክንያት የ25 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡
በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሄረሰብ ዞን በህወሃት ቁጥጥር ስር ባሉት ጻጉብጂ እና አበርገሌ ወረዳዎች እርዳታ እየደረሰ ባለመሆኑ በምግብና ህክምና እጥረት ምክንያት 25 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ሃላፊ አቶ ከፍያለው ደባሽ ለአሃዱ ገልጸዋል፡፡
ከነዚህ መካከል 5ቱ ህጻናት መሆናቸውን የገለጹት አቶ ከፍያለው የትግራይ ክልል በህወሃት ቁጥጥር ስር እንደመሆኑ የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ እርዳታ እንዲገባ እየተደረገ ቢሆንም በዞኑ በህወሃት ቁጥጥር ስር የሚገኙት ሁለት ወረዳዎች ግን እርዳታ እየተላከላቸው አይደለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ይህ አሃዝ የዞኑ ምክር ቤት ባደረገው ጉባኤ ላይ ከሰቆጣ ሆስፒታል የተገኘውን ሪፖርት መነሻ በማድረግ መገለጹን የተናገሩት ሃላፊው ቀደም ሲል በተጠቀሱት ችግሮች ምክንያት የሞቱ ሰዎች አሃዝ ሊጨምር ይችላልም ሲሉ ለአሃዱ ተናግረዋል፡፡
ካለፈው መስከረም ወር በኋላ እርዳታው እየተመናመነ ቆይቶ አሁን ላይ ምንም አይነት እርዳታ እየገባ እንዳልሆነ በማንሳት መንግስት ያለውን ችግር ተረድቶ እርዳታን ማድረስ እንዲሁም አለማቀፍ የረድኤት ድርጅቶችም እንዲገቡ መንገድ ማመቻቸት አለበት ሲሉም አክለዋል፡፡
አሃዱም ለተጨማሪ ማብራሪያ የአማራ ክልል አደጋ መከላከል ቢሮን ለማነጋገር ጥረት ቢያደርግም አልተሳካም፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahadutelevision
186 views08:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 16:59:11 እንደ ምክር ቤት አባልነታችን ከመረጠን ህዝብ ጋር የምናደርገዉ ዉይይት የሚተቸዉ ዉጤት ስለማያመጣ ሳይሆን ዉጤቱ ትኩረት ስለማይሰጠዉ ነዉ ሲሉ አባላቱ ገልጸዋል፡፡
የምክር ቤት አባላት ከመረጣቸው ማህበረሰብ ጋር የሚያደርጉት ውይይት ውጤት አያመጣም የሚለዉ እሳቤ ተገቢ አይደለም ብለዋል አሀዱ ያነጋገራቸዉ የምክር ቤት አባላት፡፡
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስራ ዘመን አሰራር መሰረት የምክር ቤት አባላት በአመት 2 ጊዜ ከመረጣቸው የማህበረሰብ ክፍል ጋር ውይይት የሚያደርጉ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ በርካታ የፖለቲካው ዘርፍ ተዋንያን ውይይቱ የህዝብ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ በር የሚከፍት ባለመሆኑ ውጤት አልባ ነው በማለት ሲገልጹ በተደጋጋሚ ይደመጣሉ፡፡
አሃዱም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በተለያዩ አካባቢዎች ከመረጣቸው ማህበረሰብ ጋር ውይይት ማድረግ መጀመራቸውን ተከትሎ የምክር ቤት አባላትን አነጋግሯል፡፡ በዚህ ዙሪያ አሃዱ ያነጋገራቸው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ክርስቲያን ታደለ በየጊዜው ከመረጠን ማህበረሰብ ጋር የምናደርገው ውይይት ውጤት አልባ ስለሆነ ሳይሆን ውይይቱ ትኩረት ስለማይሰጠውና የሚነሱ ጉዳዮችን ትኩረት ሰጥተው የሚዘግቡ መገናኛ ብዙሃን ባለመኖራቸው ነው ሲሉ ወቅሰዋል፡፡
‹‹በምንወቀሰው ልክ ውጤት አልባ አይደለንም›› ሲሉ የሚሞግቱት አቶ ክርስቲያን ከተነሱ የህዝብ ጥያቄዎች መካከል ምላሽ ያገኙ ጉዳዮችንም በማንሳት ሙሉ በሙሉ ስራ አይሰሩም የሚል ትችት መሰንዘሩ ተገቢ አይደለም ሲሉ አብራርተዋል፡፡
ሌላኛው በዚህ ዙሪያ አስተያየታቸውን የሰጡት በምክር ቤቱ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተወካይ አቶ አብዱልጀዋድ መሃመድም በበኩላቸው ‹‹ውይይቶቹ እጅግ ጠቃሚ ናቸው፣ ምላሽ ያገኙም ሆነ ያላገኙ ጉዳዮችን ሪፖርት በየጊዜው እናደርጋለን›› ብለዋል፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በየጊዜው ከመረጣቸው ማህበረሰብ ጋር ውይይት የሚያደርጉ ሲሆን ካለፈው ሳምንት ጀምሮም ወደ ተመረጡባቸው አካባቢዎች በማቅናት ውይይት እንዳደረጉም ይታወቃል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahadutelevision
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦ https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
2.4K views13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ