2023-02-24 14:48:19
ቀድሞ ከነበረው 206 ጽህፈት ቤቱ ዉስጥ አሁን ላይ 4 ብቻ እንደቀሩ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ ) አስታወቀ፡፡
የሸኔ ቡድን ዘርፈ ብዙ ጉዳት እያደረሰ ስለመሆኑ በመንግስት አካላት ቢነገርም በንጹሃን ዜጎች ላይ ግን ጥቃት የምፈጽመው እኔ አይደለሁም በማለት ሲያስተባብል ይስተዋላል፡፡
ይሄን በተመለከተ እውነታው ምንድነው የማጣራት ስራስ ተሰርቷል ወይ የሚል ጥያቄ በትላንትናው እለት በአሃዱ መድረክ ላይ ለተገኙት ኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጥርነህ ገምታ ተነስቶላቸዋል፡፡ በምላሻቸውም እኛም እንደሌላው ሰው በወሬ ደረጃ የምንሰማው እንጂ እርግጠኛ ሆነን በዚህ ጉዳይ ላይ ምላሽ መስጠት የሚያስችል ማረጋገጫ የለንም ነዉ ያሉት፡፡
ጉዳዩን አለም አቀፍም ሆነ ሀገር አቀፍ ገለልተኛ ቡድን ሊያጣራው እንደሚገባ የተናገሩት አቶ ጥሩነህ ሰላም ፤ዲሞክራሲ በሌለበት የፖለቲካ ምህዳሩ ጠባብ በሆነበት ሀገር ላይ አምጸው የትጥቅ ትግል የሚያደርጉም እንዳሉ እና በኢትዮጵያ የተጀመረ እንዳልሆነም አንስተዋል፡፡
የፖለቲካ ምህዳሩ መጥበብ አስቸጋሪ ወይም እንቅፋት ከሆነባቸው ፓርቲዎች በካከል አንዱ የኦሮሚያ ፌደራልሲት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ነው ያሉት ዋና ጸሀፊው ፓርቲው ቀድሞ ከነበረው 206 ጽህፈት ቤቱ አሁን ላይ 4 ብቻ እንደቀሩት ተናግረዋል፡፡
ከ206 ጽህፈት ቤቱ 4 ብቻ መቅረቱ የሚያሳየው የፖለቲካ ምህዳሩ መጥበብን እንደሆነ አንስተው ጽህፈት ቤቶቹ በመንግስት አካላት ተሰብረው የተዘረፉ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ደግሞ ፓርቲው እየደረሰበት ካለው ተጽኖ አንጸር የተዘጉ ናቸው ብለዋል፡፡
ሀገሪቱ እስካሁን ድረስ ከግጭት እና ጦርነት አልወጣችም ያሉት ዋና ጸሃፊዉ ሰላምን ለማምጣት የሚደረገውን ስምምነት ፓርቲው እንደሚደግፈዉም ጠቁመዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahadutelevision
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦ https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_2
2.6K views11:48