Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ክልል የሚገኙት ሼባ ሌዘር እና ሰማያት የእምነበረድ ፋብሪካ ሙሉ ለሙሉ እንደወደሙና ሰራተ | AHADU RADIO FM 94.3

በትግራይ ክልል የሚገኙት ሼባ ሌዘር እና ሰማያት የእምነበረድ ፋብሪካ ሙሉ ለሙሉ እንደወደሙና ሰራተኞቹ የት እንዳሉ እንደማይታወቅ የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌድሬሽን አስታወቀ፡፡
በትግራይ ክልል ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ክልሉ የተጎዘዉ የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌድሬሽን በክልሉ ቅርንጫፍ ፅፈት ቤት እና ከ70 ሺ በላይ አባል ያለዉ ሲሆን በክልሉ ባደረገዉ ጉብኝት ሼባ ሌዘር እና ሰማያት የእምነበረድ ፋብሪካን ሙሉ ለሙሉ መዉደማቸዉን መመልከት እንደቻሉ የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌድሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሰሁን ፎሎ ለአሀዱ ተናግረዋል፡፡

አንደኛዉ ፋብሪካ 1200 ሰራተኞች ያሉት ሲሆን ሌላኛዉ ፋብሪካ ደግሞ 600 ሰራተኛ የያዘ መሆኑን ገልፀዉ ሆኖም ግን በአሁኑ ሰአት ሰራተኞች የት እንዳሉ እንደማያዉቁ የፋብሪካዎቹ አመራሮች እንደገለፁላቸዉ አስታዉቀዋል፡፡

ሁለቱ ፋብሪካዎች ሙሉ ለሙሉ በመዉደማቸዉ ምክንያት በድጋሚ ስራ ለመጀመር አደጋች መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም አልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ሙሉ ለሙሉ መዉደሙን እና ከምእራብ ትግራይ ከወልቃይት ስኳር ፋብሪካ እና ከህይወት እርሻ መካናይዜሽን ተፈናቅለዉ መቀሌ የሚገኙ ሰራተኞች መኖራቸዉን ተናግረዋል፡፡

መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ እና አዲግራት መድሀኒት ፋብሪካ በከፊል ስራ መጀመራቸዉን አቶ ካሳሁን አስታዉቀዋል፡፡
ስራ ያልጀመሩ ፋብሪካዎች ተጠግነዉ ስራ መጀመር አንዲችሉ በክልሉ መንግስት እና በፌደራል መንግስቱ በኩል ድጋፍ ሊደረግላቸዉ ይገባል ነዉ ያሉት፡፡
ስራ በጀመሩ ፋብሪካዎች ዉስጥ ለሚሰሩ ሰራተኞች የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌድሬሽን ስልጠና እንደሚሰጥ አቶ ካሳሁን አክለዉ ተናግረዋል፡፡