Get Mystery Box with random crypto!

በሃገሪቱ በርካታ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ እየተባባሰ መምጣቱን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ ካ | AHADU RADIO FM 94.3

በሃገሪቱ በርካታ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ እየተባባሰ መምጣቱን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
ካለፈው አመት አጋማሽ አንስቶ በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ በተለይም በኦሮምያ ፣ ሱማሌ ፣ አፋር ፣ ደቡብና ደቡብ ምእራብ ክልሎች ከፍተኛ ጉዳትን ያስከተለ ሲሆን በተለይም የኦሮምያና ሱማሌ ክልል አርብቶ አደር አካባቢዎች ከፍተኛው ጉዳት የተመዘገበባቸው አካባቢዎች እንደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
አሃዱም ጉዳዩ በዋነኝነት የሚመለከተው የግብርና ሚኒስቴር ድርቁን በተመለከተ መረጃን በቶሎ ለህዝብ የማይገልጽ መሆኑን ተከትሎ ምን እየሰራችሁ ትገኛላችሁ ሲል ጥያቄ አቅርቧል፡፡
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የእንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪው ዶክተር ዮሃንስ ግርማም ድርቁ ሰፋፊ የአርብቶ አደር አካባቢዎች ላይ እየከፋ መምጣቱን ተከትሎ ለአርብቶ አደሮች የእንስሳት መኖን የማቅረብ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
በተለይም ድርቁ በከፍተኛ ሁኔታ ያጠቃቸው በኦሮምያ ክልል ቦረና ዞን እንዲሁም በሶማሌ ክልል ዳዋ ዞን መኖን በከፍተኛ መጠን በማቅረብ የእንስሳቱን ብሎም የአርብቶ አደሩን ህይወት ለመታደግ ጥረት እያደረግን ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡
እስካሁን ባለው ሁኔታ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ እንስሳት በድርቁ ምክንያት መሞታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችና ሌሎች ምንጮች በተደጋጋሚ እየገለጹ ቢሆንም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ግን አሃዙን ከመግለጽ ተቆጥቧል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahadutelevision