Get Mystery Box with random crypto!

ድርቅ በተከሰተባቸው የሀገራችን አካባቢዎች የሚገኙ ብሄራዊ ፓርኮች ውስጥ ያሉ የዱር እንስሳት ከፍተ | AHADU RADIO FM 94.3

ድርቅ በተከሰተባቸው የሀገራችን አካባቢዎች የሚገኙ ብሄራዊ ፓርኮች ውስጥ ያሉ የዱር እንስሳት ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደሚገኙ ተገለፀ፡፡

በሀገራችን የተወሰኑ አካባቢዎች ላይ የተከሰተው ድርቅ በአካባቢው ከሚኖረው የማህበረሰብ ክፍል በተጨማሪም በእነዚሁ አካባቢዎች አቅራቢያ የሚገኙት ሁለት ብሄራዊ ፓርኮች ከፍተኛ አደጋ ላይ እንዲወድቁ ማድረጉን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የኮምዩኒኬሽን ባለሙያ አቶ ናቃቸው ብርሌ አስታውቀዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በዋናነት ከፍተኛ ስጋት ያለበት የቦረና ብሄራዊ ፓርክ ሲሆን ሌላኛው በድርቁ ምክንያት ስጋት ላይ የሚገኘው ደግሞ በራህሌ ብሄራዊ ፓርክ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ እንደ የሜዳ አህያ ፣ ከርከሮ እና ሌሎችም በቦረና ብሄራዊ ፓርክ ውስጥ የሚገኙ የዱር እንሰሳት በድርቁ ምክንያት አደጋ የተደቀነባቸው እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ ድርቅ ለደረሰባቸው አካባቢዎች የተሰጠው ትኩረት እና ድጋፍ የሚበረታታ ቢሆንም ለፓርኮች እና ለዱር እንስሳቱ የተሰጠው ትኩረት ግን ዝቅተኛ እንደሆነ ገልጸው አሁን ላይ ከክልሉ ደን እና የዱር እንስሳት ድርጅት እንዲሁም የዱር እንስሳት ላይ ትኩረታቸውን አድርገው ከሚሰሩ አለማቀፍ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ውሃ እና መኖ እንዲቀርብላቸው እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡
አክለውም በእነዚህ አካባቢዎች ያሉ የዱር እንስሳትን ለመታደግ በቅድሚያ ማህበረሰቡን መታደግ ዋነኛዉ እንደመሆኑ መጠን ከሚመለከታቸዉ ተቋማት ጋር በመተባበር ለማህበረሰቡ የተለያዩ የምግብ እና አስቸኳይ እርዳታዎች ድጋፍ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision