Get Mystery Box with random crypto!

የስነ ምግባር ጉድለት ባሳዩ እና በብልሹ አሰራር ላይ በተሳተፉ 109 ሰራተኞች ላይ እርምጃ እንደተ | AHADU RADIO FM 94.3

የስነ ምግባር ጉድለት ባሳዩ እና በብልሹ አሰራር ላይ በተሳተፉ 109 ሰራተኞች ላይ እርምጃ እንደተወሰደባቸዉ ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አሌክትሪክ አገልግሎት ባለፉት 6 ወራት የስነ ምግባር ጉድለት ባለባቸዉ በሙስና እና በብልሹ አሰራር ላይ በተሰማሩ 109 ሰራተኞች ላይ እርምጃ መወሰዱን አስታዉቋል፡፡
ከነዚህ ሰራተኞች መካከል 15 የሚሆኑ ሰራተኞች ከስራ እንዲሰናበቱ መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አሌክትሪክ አገልግሎት የእቅድ ዝግጅት ክፍል ስራ አስፈፃሚ አቶ አወል ካሳ ተናግረዋል፡፡

16 የሚሆኑ አመራሮች ከሀላፊነት እንዲነሱ መደረጉን ገልፀዉ በሌሎቹ ላይ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን አስታዉቀዋል፡፡
የክፍያ ጊዜን ለደንበኛዉ በወቅቱ ከማሳወቅ አንፃር ያሉ የአሰራር ክፍተቶችን በማሻሻል የተጠያቂነትን ለማስፈን በትኩረት እየሰሩ መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡
ህግና ስርዓትን በመጣስ ተገልጋይን የሚያጉላሉ ሰራተኞች ላይ አስፈላጊዉን እርምጃ ለመዉሰድ ቁርጠኛ መሆናቸዉን አቶ አወል አክለዉ ተናግረዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahadutelevision
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦ https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24