Get Mystery Box with random crypto!

በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን የሚገኙ ስድስት አባላቱ ያለአግባብ እንደታሰሩበት ኢዜማ አስታወቀ፡፡ የኢ | AHADU RADIO FM 94.3

በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን የሚገኙ ስድስት አባላቱ ያለአግባብ እንደታሰሩበት ኢዜማ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ኢዜማ አምስት የደቡብ ክልል ምክር ቤት አባላቱን ጨምሮ ስድስት የፓርቲዉ አባላት ያለአግባብ በመታሰራቸዉ መንግሥት በአስቸኳይ እንዲፈታቸዉ ሲል ጠይቁዋል፡፡
የኢዜማ የህግና የአባላት ደህንነት ጉዳይ መምሪያ ሃላፊ አቶ ስዩም መንገሻ ለአሀዱ እንደተናገሩት አባላቶቹ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ተይዘዉ መታሰራቸዉን አስታዉቀዋል፡፡

የታሳሩት የፓርቲዉ አባላት ከየካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በእሥር ላይ እንደቆዩና በሕጉ መሠረት 48 ሰዓት ፍርድ ቤት መቅረብ ሲገባቸው እስካሁን ድረስ ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ ገልፀዋል፡፡
አባላቱ የተከሰሱበት ጉዳይ እንዳልታወቀ ገልጸዉ በዚህም ምክንያት በአባላቱ ላይ የህገ መንግሥት ጥሰት እየተፈጸመባቸው ይገኛል ነዉ ያሉት፡፡

ለደቡብ ክልል ፍትህ ቢሮ ፣ ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እና ለፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትን ጨምሮ ለተለያዩ አካላት ጥያቂያቸዉን በደብዳቤ ማቅረባቸዉን አቶ ስዩም አክለዉ ተናግረዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahadutelevision
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦ https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24