Get Mystery Box with random crypto!

ከዚህ ቀደም ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ በአንድ አመት የጊዜ ሂደት ይሰበሰብ የነበረውን ገንዘብ | AHADU RADIO FM 94.3

ከዚህ ቀደም ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ በአንድ አመት የጊዜ ሂደት ይሰበሰብ የነበረውን ገንዘብ በሰባት ወር ውስጥ መሰብሰብ እንደተቻለ ተገለጸ፡፡
ምንም እንኳን በሀገራችን ያለው ነባራዊ እውነታ በብዙ መልኩ አመቺነት ባይኖረውም ከመቼውም ጊዜ በላይ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል ገንዘብ ከህብረተሰቡ መሰብሰብ መቻሉን በማስታወስ በዘንድሮው አመት ባለፉት ሰባት ወራቶች ብቻ ከ948 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የገለጹት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤ የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሀይሉ አብርሃም የህዳሴው ዋንጫ ባለፉት ስድስት ወራት በመላ ሀገሪቱ ባይዞርም ህብረተሰቡ ግን በሌሎች መንገዶች ድጋፉን በመቀጠሉ ገቢው ከፍ እንዲል ማድረግ ማስቻሉን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
የገቢ መጠኑን ከዚህም በላይ ለማሳደግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ አክልው የገለጹት አቶ ሀይሉ የህዳሴው ግድብ 12ተኛ አመት ክብረ በአልን አስመልክቶም የተለያዩ ሁነቶችን በማዘጋጀት እና ህብረተሰቡን ተሳታፊ በማድረግ ገቢውን ለመጨመር ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ተግባር ለመግባት በሂደት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረ የፊታችን መጋቢት 24 ቀን 2015 ዓ/ም ድፍን አስራ ሁለት አመታት እንደሚሆነው ይታወቃል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24