Get Mystery Box with random crypto!

ባለፉት 6 ወራት ከ200 ሺህ በላይ ነዋሪዎች የዲጅታል መታወቂያ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸዉ ተገለ | AHADU RADIO FM 94.3

ባለፉት 6 ወራት ከ200 ሺህ በላይ ነዋሪዎች የዲጅታል መታወቂያ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸዉ ተገለፀ፡
በአዲስ አበባ ከተማ 118 ወረዳዎች የሚገኙ ሲሆን 104 ወረዳዎች ዲጂታል አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ እየሰጡ መሆናቸዉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ አስታዉቋል፡፡
ቀሪዎቹ 14 ወረዳዎች ንፋስ ስልክ ላፍቶ፤ አቃቂ እና በለሚኩራ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ወረዳዎች ሲሆን የመሰረተ ልማት ግንባታ እየተከናወነላቸዉ መሆኑን በምክትል ዋና ዳይሬክተር ማዕረግ የኤጀንሲዉ አማካሪ አቶ መላክ መኮንን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
በቅርቡ እነዚህ 14 ወረዳዎች እየተከናወነ ያለዉ የመሰረተ ልማት ግንባታ ሲጠናቀቅ ዲጅታል አገልግሎቱን ይስጣሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡
የዲጅታል አገልግሎቱ ብልሹ አሰራርን ለመከላከል እንደሚያስችል ገልፀዉ ባለፉት 6 ወራት ከ200ሺህ በላይ ነዋሪዎች የዲጅታል መታወቂያ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸዉን አስታዉቀዋል፡፡
በህመም ላይ ላሉ ዜጎች በልዩ ሁኔታ የማኑዋል አገልግሎት ተፈቅዶ የቤት ለቤት አገልግሎት እየተሰጣቸዉ መሆኑን አቶ መላክ አክለዉ ተናግረዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahadutelevision
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24