Get Mystery Box with random crypto!

እንስሳት ከአንድ አካባቢ ወደ ሌላ አካባቢ ሲንቀሳቀሱ የሚጠቀሙባቸው የምገባ ማእከላት መዘጋጀታቸው | AHADU RADIO FM 94.3

እንስሳት ከአንድ አካባቢ ወደ ሌላ አካባቢ ሲንቀሳቀሱ የሚጠቀሙባቸው የምገባ ማእከላት መዘጋጀታቸው ተገለጸ፡፡

ይህንን ያሉት በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪው ዶክተር የሃንስ ግርማ ሲሆኑ ድርቁ በከፋባቸው አካባቢዎች ያሉ አርብቶ አደሮች ቀያቸዉን ለቀው ለእንስሳቱ የሚሆን የግጦሽ ሳር ወደ አለባቸው ቦታዎች እንደሚሄዱ ተናግረዋል፡፡

በአንዳንድ አካባቢዎች ያሉ አርብቶ አደሮች እንደ ኬንያና ሱዳን ያሉ አጎራባች ሃገራትን ተሻግረው ቢሄዱም እነሱም በድርቅ የተጠቁ በመሆናቸው የተሻለ ነው ያልነዉን የእንስሳት ምገባ ማእከልን ተደራሽ የማድረግ አማራጭ ወስደናል ነው ያሉት፡፡
በአብዛኛው ከተለያዩ አካባቢዎች እንስሳቶቻቸውን ይዘው የሚንቀሳቀሱ አርብቶ አደሮች ወደ ኦሮምያና ደቡብ ክልል የግጦሽ ሳር በብዛት የሚገኝባቸው ቦታዎች ይዘው እንደሚሄዱ የገለጹት አማካሪው በእነዚሁ አካባቢዎች ማእከላቱ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ከክልልና ዞን ቢሮዎች ጋር መወያታቸውን ተናግረዋል ፡፡

አንዳንድ የኢትዮጵያ፣ የሶማሊያ እና የኬንያ አካባቢዎች ለአምስት ተከታታይ ወቅቶች ዝናብ አለማግኘታቸውን ተከትሎ ሚሊዮኖችን ለምግብ እጥረት እንደሚያጋልጥ ዓለም አቀፍ ተቋማት ሲያሳስቡ ቆይተዋል።
የተለያዩ የአገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በአሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ ሲገልጹ የዓለም ጤና ድርጅትም አሃዙን 24 ሚሊዮን ስለመድረሱ መግለጹ አይዘነጋም።

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP