Get Mystery Box with random crypto!

በዋግ ኽምራ ዞን በእርዳታ እጥረትና በህክምና እጦት ምክንያት የ25 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡ | AHADU RADIO FM 94.3

በዋግ ኽምራ ዞን በእርዳታ እጥረትና በህክምና እጦት ምክንያት የ25 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡
በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሄረሰብ ዞን በህወሃት ቁጥጥር ስር ባሉት ጻጉብጂ እና አበርገሌ ወረዳዎች እርዳታ እየደረሰ ባለመሆኑ በምግብና ህክምና እጥረት ምክንያት 25 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ሃላፊ አቶ ከፍያለው ደባሽ ለአሃዱ ገልጸዋል፡፡
ከነዚህ መካከል 5ቱ ህጻናት መሆናቸውን የገለጹት አቶ ከፍያለው የትግራይ ክልል በህወሃት ቁጥጥር ስር እንደመሆኑ የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ እርዳታ እንዲገባ እየተደረገ ቢሆንም በዞኑ በህወሃት ቁጥጥር ስር የሚገኙት ሁለት ወረዳዎች ግን እርዳታ እየተላከላቸው አይደለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ይህ አሃዝ የዞኑ ምክር ቤት ባደረገው ጉባኤ ላይ ከሰቆጣ ሆስፒታል የተገኘውን ሪፖርት መነሻ በማድረግ መገለጹን የተናገሩት ሃላፊው ቀደም ሲል በተጠቀሱት ችግሮች ምክንያት የሞቱ ሰዎች አሃዝ ሊጨምር ይችላልም ሲሉ ለአሃዱ ተናግረዋል፡፡
ካለፈው መስከረም ወር በኋላ እርዳታው እየተመናመነ ቆይቶ አሁን ላይ ምንም አይነት እርዳታ እየገባ እንዳልሆነ በማንሳት መንግስት ያለውን ችግር ተረድቶ እርዳታን ማድረስ እንዲሁም አለማቀፍ የረድኤት ድርጅቶችም እንዲገቡ መንገድ ማመቻቸት አለበት ሲሉም አክለዋል፡፡
አሃዱም ለተጨማሪ ማብራሪያ የአማራ ክልል አደጋ መከላከል ቢሮን ለማነጋገር ጥረት ቢያደርግም አልተሳካም፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahadutelevision