Get Mystery Box with random crypto!

እንደ ምክር ቤት አባልነታችን ከመረጠን ህዝብ ጋር የምናደርገዉ ዉይይት የሚተቸዉ ዉጤት ስለማያመጣ | AHADU RADIO FM 94.3

እንደ ምክር ቤት አባልነታችን ከመረጠን ህዝብ ጋር የምናደርገዉ ዉይይት የሚተቸዉ ዉጤት ስለማያመጣ ሳይሆን ዉጤቱ ትኩረት ስለማይሰጠዉ ነዉ ሲሉ አባላቱ ገልጸዋል፡፡
የምክር ቤት አባላት ከመረጣቸው ማህበረሰብ ጋር የሚያደርጉት ውይይት ውጤት አያመጣም የሚለዉ እሳቤ ተገቢ አይደለም ብለዋል አሀዱ ያነጋገራቸዉ የምክር ቤት አባላት፡፡
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስራ ዘመን አሰራር መሰረት የምክር ቤት አባላት በአመት 2 ጊዜ ከመረጣቸው የማህበረሰብ ክፍል ጋር ውይይት የሚያደርጉ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ በርካታ የፖለቲካው ዘርፍ ተዋንያን ውይይቱ የህዝብ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ በር የሚከፍት ባለመሆኑ ውጤት አልባ ነው በማለት ሲገልጹ በተደጋጋሚ ይደመጣሉ፡፡
አሃዱም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በተለያዩ አካባቢዎች ከመረጣቸው ማህበረሰብ ጋር ውይይት ማድረግ መጀመራቸውን ተከትሎ የምክር ቤት አባላትን አነጋግሯል፡፡ በዚህ ዙሪያ አሃዱ ያነጋገራቸው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ክርስቲያን ታደለ በየጊዜው ከመረጠን ማህበረሰብ ጋር የምናደርገው ውይይት ውጤት አልባ ስለሆነ ሳይሆን ውይይቱ ትኩረት ስለማይሰጠውና የሚነሱ ጉዳዮችን ትኩረት ሰጥተው የሚዘግቡ መገናኛ ብዙሃን ባለመኖራቸው ነው ሲሉ ወቅሰዋል፡፡
‹‹በምንወቀሰው ልክ ውጤት አልባ አይደለንም›› ሲሉ የሚሞግቱት አቶ ክርስቲያን ከተነሱ የህዝብ ጥያቄዎች መካከል ምላሽ ያገኙ ጉዳዮችንም በማንሳት ሙሉ በሙሉ ስራ አይሰሩም የሚል ትችት መሰንዘሩ ተገቢ አይደለም ሲሉ አብራርተዋል፡፡
ሌላኛው በዚህ ዙሪያ አስተያየታቸውን የሰጡት በምክር ቤቱ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተወካይ አቶ አብዱልጀዋድ መሃመድም በበኩላቸው ‹‹ውይይቶቹ እጅግ ጠቃሚ ናቸው፣ ምላሽ ያገኙም ሆነ ያላገኙ ጉዳዮችን ሪፖርት በየጊዜው እናደርጋለን›› ብለዋል፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በየጊዜው ከመረጣቸው ማህበረሰብ ጋር ውይይት የሚያደርጉ ሲሆን ካለፈው ሳምንት ጀምሮም ወደ ተመረጡባቸው አካባቢዎች በማቅናት ውይይት እንዳደረጉም ይታወቃል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahadutelevision
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦ https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24